ኮቪድ - 19 ላይ ተጨማሪ ገጾች

Share This article:

አጠቃላይ እይታ

መንግስታት የኮቪድ – 19 ስርጭትን ለመቆጣጠር በቤት ውስጥ መቀመጥን እና እራስን ለይቶ ማቆየትን የሚያስገድዱ እርምጃዎችን እየወሰዱ ሲሆኑ፥ እነዚህ እርምጃዎች በማህበረሰቡ ላይ ሊፈጥሩ የሚችሉትን የስነልቦና ቀውስ ትኩረት አልሰጡትም፡፡ በተለይም በዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸዉ ሃገሮች፥ በጣም ዝቅተኛ እለታዊ ገቢ ያላቸው ሕብረተሰቦች ከግማሽ በላይ የህዝብ ቁጥር ይይዛል፥ የገቢ ምንጫቸውን በኮቪድ-19 ምክኒያት የተቅዋረጠዉ እነዚህ ህዝቦች በቫይረሱ ከመያዝ በላይ በረሃብ መሞትን ፥ ከቤት መፈናቀልን ይፈራሉ፡፡
ከገቢ መቃወስና መሰረታዊ ፍላጎት የሆኑትን ምግብና ውሃ ማጣት የፈጠረው ፍርሃት: ውጥረት: ጭንቀት እና ብቸኝነት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ይሰማል፡፡ በመንግስት ከሚደረግ የገንዘብ ድጋፍ፥ ከቀጣሪዎች ያልተቋረጠ ክፍያ እና የበጎ ፈቃደኞች አገልግሎት ባሻገር በስነልቦና እና የአእምሮ ጤና ላይ የሚደርሰውን ጉዳት መከላከል የማህበረሰቡን ህልውና ለማስቀጠል ወሳኝ ነው፡፡ በዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገሮች ውስጥ የአእምሮ ህመም ከፍተኛ ጫና ቢኖርባቸውም ፣ ለአእምሮ ጤና እንክብካቤን የሚመደቡ የሰው እና የገንዘብ ሀብቶች እጅግ በጣም አነስተኛ ስለሆኑ፣ ማኅበረሰቡ የራሱን የስነ-ልቦና ጫና እራሱ እንዲቋቋም ግዴታ ጥሎበታል፡፡

የሚከተሉትን ምክሮች በመተግበር በእርስዎና ቤተሰብዎ ላይ ሊደርስ የሚችለውን ውጥረት ይቀንሱ፡፡

ውጤታማ የስነልቦና ጫናን መቋቋሚያ ስልቶች

ነቀፋ የሌለበት አካባቢ ይፍጠሩ

በ ኮቪድ – 19 ወረርሽኝ ምክንያት የተፈጠሩትን ስሜቶች ለመቋቋም የመጀመሪያው እርምጃ አሁን ባለዎት ሁኔታ ተጠያቂ እንደማይሆኑ ማወቅ ነው፡፡የስራዎ ማጣት ይሁን አሊያም ከባድ የጤና ችግር ያለባቸው አዛውንት ወላጅዎ የሰዎችን ግንኙነት የመቀነስ አስፈላጊነት አለመገንዘባቸውን ፣ ወይም ልጆችዎ ቀኑን ሙሉ በቤቱ ውስጥ እንዳይታሰሩ በመጨነቅ ፤ እራሶን መውቀስ አስፈላጊ አይደለም፡፡ የሥነ ልቦና ባለሙያ እና ደራሲ የሆኑት ዶክተር ሃሪሌነር እንደገለጹት፤ እንደተጨነቅን ሆኖ ሲሰማን እራሳችንን “ደካሞች” ወይም እራሳችንን ከሌሎች ጋር ማነፃፀር ሁኔታችንን ሊያባብ ሰው ይችላል፡፡

አይፍሩ፣ስሜትዎን ይግለጹ

ከጎረቤት ሆነ ፣ ከስራ ባልደረባ፣ወይም ከልጅዎ ትምህርት ቤት ወላጆች ኮሚቴ አባል፣ ጋር ቢያንስ አንድ ተመሳሳይ የሆነ የሕይወት ሁኔታዊ ውጥረትን በመካፈለዎ ለሌላ ሰው ሁኔታዎትን ማጋራቱ በከፍተኛ ደረጃ ጠቃሚ ይሆናል፡፡ የጋራ ጠላት ፣ በሆነዉ በ ኮቪድ – 19 መጠቃት፤ አንዱ ወደአንዱ ለመዞር እና ለእርዳታ እና መመሪያን ለመጠየቅ አግባብ ጊዜ ይህ ነው። ምናልባት ጎረቤትዎ ልጆችዎን እንዴት  በሥራ እንዲጠመዱ ማድረግን ሊያካፍለዎት ይችል ይሆናል፣የሥራ ባልደረባዎ እርስዎ ሊያመለክቱበት የሚገባ የማህበራዊ ድጎማ ጥቅማጥቅሞችን ሲሰሙ አጋጣሚዉን ተጠቅም ሊነግሮት ይችላል ፣ ምናልባትም የወላጆች ኮሚቴ አንድ አባል  ልጆች ከበሽታው ጋር ሊከሰት የሚችለዉን የስነልቦና ጫና መቋቋም የሚችሉበትን  ውጤታማ መንገድ ለማጋራት ፍቃደኛ ሊሆኑ ይችላሉና ፤ አንዱ ከሌላው መማር በዚህ ወረርሽኝ ወቅት ጭንቀት የሚፈጥሩትን ችግሮች ለመፍታት ጥሩ መንገድ ነው፡፡ከሚወዷቸው ሰዎች እና ከቅርብ ጓደኞችዎ ማህበራዊ ድጋፍን በመፈለግ በአካባቢዎ ካሉ ሰዎች ጋር ያለዎትን ግንኙነት ማቀራረብ ብቻ ሳይሆን ሌሎችምንም ችግሮችን በቀላሉ እንዲቋቋሙ ይረዳቸዋል፡፡ ችግሮቻቸውን መፍታት የለብዎትም። ከአጠገባቸው መሆኖንና ችግራቸዉን እርሶም እንደሚካፈሉ ማሳወቁ ከምንም በላይ ለሁሉም ይረዳል።

ቤተሰብዎ ስለ ኮቪድ - 19 ወረርሽኝ እንዲገነዘቡ ማገዝ

ከአረጋዊ ወላጆችህ ጋር መነጋገር

ብዙ ወላጆች፣በተለይም የአፍሪካ ወላጆች ፣ ስለ COVID-19፤ ስለሚያደርጉት ጥንቃቄ የልጆቻቸውን ምክር ለመስማት ይቸገራሉ፡፡ብዙ አፍሪቃውያን ወላጆች ልጆች መመሪያዎችን ከወላጆች መቀበል እንጂ ለመስጠትከወላጆች በላይ እዉቀት አላቸዉ ብለዉ አያምኑም፡ ፡ምክንያቱም አብዛኛው የአፍሪካ ባህል ፤ እውቀት ከእድሜ ጋር ይመጣል የሚል እምነት ስላለው፣የአንድን ሽማግሌ ዕውቀት እና ልምዶች ከልጆቻቸው ይልቅ የተሻሉ ውሳኔ ሰጭዎች ያደርጋቸዋል ተብሎ ይገመታል፡፡የኮቪድ – 19 ስርጭትን የመከላከል ህጎችን መከተል በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምን እንደሆነ በዕድሜ የገፉ ወላጆች ከእድሜያቸው አጋር ወይም ከሃይማኖት መሪ ጋር እንዲነጋገሩ ያድርጉ፡፡

ከልጆችዎ ጋር ማውራት

የልጅዎን ዕድሜ ከግምት ውስጥ በማስገባት ፣ ስለ ኮቪድ -19 ያሉ እውነታዎችን እና ዝርዝሮችን ለማቅረብ ልጆች ሊረዷቸው የሚችሏቸውን ቃላት ይጠቀሙ። ተገቢ እና ትክክለኛ ቃላትን በመጠቀም ፤ ቀላል ፣ ግልፅ እና አፅናኝ በሆነ መንገድ ያናግሯቸው፡፡ ምን እንደሚያውቁ እና አሁን ስላለው ሁኔታ ምን እንደሚሰማቸው በመጠየቅ ይጀምሩ። ብዙ መረጃዎች ጭንቀትን ሊፈጥሩ ስለሚችሉ ውይይቱን እንዲመሩ ያድርጓቸው፡፡ ፍርሃታቸውን በመገንዘብ፤ ታማኝ ሁኑላቸው::

ለትንንሽ ልጆች እንዴት ስለ ኮቪድ -19 ማስረዳትእንደሚቻል የሚያስረዳ፡በወላጅ ትምህርት አሰልጣኝ ሊንዳሀርድፊልድ ምንጭ-https://www.unicef.org/jamaica/stories/use-covid-19-build-better-family- Communication

“ኮሮና ቫይረስ የጀርም ዓይነት ነው፡፡ እነዚህ ጀርሞች በጣም ጥቃቅን ናቸው። እነዚህ ጀርሞች ወደሰውነታችን ውስጥ ሲገቡ በሽታ ያሲዙናል። ጀርሞች በአፍንጫችን ፣ በአፋችን ወይም በአይናችን ወደ ሰውነታችን ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ ፡፡ አንድ ሰው እጁ ላይ ካሳለ በኋላ በእጁ የበር እጄታ ጨብጦ ሌላ ሰው መጥቶ ያንን የበር እጄታ ቢነካው፤ የበሩን እጄታ የነካው ሁለተኛ ሰውዬ ሰውነት ውስጥ ጀርሞች ሊገቡ ይችላሉ። እጆቻችንን በተደጋጋሚ መታጠብና ብዙ ሰው የሚበዛበት ቦታ አለመሄድ በበሽታ ከመጠቃት ይከላከላሉ”

ልጆችን ስለኮቪድ – 19 በተረት ተረት ማስተማር ይቻላል።የእንግሊዝኛ ኮቪድ – 19 ተረቶችን ከፈለጉ ይሄንን ይጫኑት ተረት  

በተጨማሪም ልጆችን ስለኮቪድ – 19 ለማስተማር የመማሪያ ቪዲዮዎችን መጠቀም ይችላሉ፡፡ ብራኢን ጶፕ አጠር ያሉ ለህፃናት የሚሆኑ ቪዲዮዎች አሉት። ይሄን በመጫን ሊያዩት ይችላሉ: ቪድዮ

ከታች ተጨማሪ ለልጆች የሚሆን ቪዲዮ ይመልከቱ.

Play Video

ዩኒሴፍ (UNICEF) ልጆች ላሏቸው ቤተሰቦች የሚከተለውን ምክር ይሰጣል:(https://www.unicef.org/coronavirus/how-talk-your-child-about-coronavirus-covid-19):

በኮቪድ-19 ጊዜ ጤነኛ ሕይወትን መምራት እንዴት ይቻላል?

በኮቪድ-19 ጊዜ ጤናማ የኑሮ ስልትን መምራት ለእርስዎም አቅራቢያዎ ላሉ ሰዎችም ጠቀሜታ ይኖረዋል። ጤናማ ኑሮ መምራት ሰውነቶ በሽታን ለመቋቋም ከማስቻሉም በላይ ለማንኛውም ለሚከሰት ችግር በቂ ምላሽ ለመስጠት ይስችልዎታል።

ጤናማ ኑሮ መምራት ማለት የሚከተሉትን ያካትታል:-

⇒ የሰውነቶን የበሽታ የመቋቋም ኃይል የሚጨምሩ ምግቦች ዝርዝር Dr. Bansal’s Homeopathy, Herbal & Lifestyle Clinic የሚባለውን ድህረ ገፅ ይጎብኙ 

⇒ከልጆችዎ ጋር አብረው ሊጫወቱ የሚችሉትን ጨዋታዎች እዚህ ጋር ማየት ይችላሉ።

የሌተቀን ውሎዎ

በኮቪድ-19 ምክንያት ቤት ከመዋሎ በፊት የነበሮትን መደበኛ ውሎ አሁንም ይቀጥሉ። ድሮውንም መደበኛ ውሎ ካልነበሮት የሚከተሉትን እርምጃዎች በመከተል የቀን በቀን ፕሮግራሞን ያውጡ።

1. የቀን/የሳምንት እቅድ

 

 

በቀን ውስጥ ምን ማድረግ እንደሚፈልጉና ካለዎት ጊዜ ምን ያህሉን መመደብ እንደሚፈልጉ ያስቡ::

 

ማንበብ፣ቴለቪዥን ማየት፣የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣በማህበራዊ ድረገጽ ላይ የሚወጡ ፈታኝ ጥያቄዎች ላይ መሳተፍ፣አየር ወደሳምባችን እያስገባን የማስወጣት እንቅስቃሴ ማድረግ፣እራስን በሚያዝናኑ ስራዎች መሳተፍ ወይም አዳዲስ መስራት በምንፈልጋቸው ነገሮችን ማካሄድ ጥቂት በየቀኑ ለመስራት ከምናቅዳቸው ስራዎች ማካተት የምንችላቸው ተግባራት ናቸው፡፡

ከቤተሰብዎ ጋር ሊያደርጓቸው ለሚችሏቸው የቤት ውስጥ እንቅስቃሴዎች ዥርዥር ይህንን ድህረ ገፅ ይጎብኙ፡፡

ይህ የቤት ቆይታ ጊዜ ከዚህ በፊት ያቀድናቸውና በተለያዩ ምክንያት ለሌላ ጊዜ ቀጠሮ የያዝንላቸውን ተግባራት ለማከናወን ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡ ለረጅም ጊዜ መደወል ያስብናቸው ስልኮች ካሉ፣ቤታችን ውስጥ መጠገን ያለባቸው እቃዎች ካሉ፣ቤታችንን በደምብ ለማጽዳት፣በቂ እንቅልፍ ለማግኘት፣ለመስራት ስንመኛቸው የነበሩ ስራዎች ላይ ጥናት ለማድረግ፣ከልጆቻችን ጋር ጊዜ ለማሳለፍ፣ወደፊት ለመስራት ያቀድናቸውን ስራዎች ለመስራት ወይም አስፈላጊ ናቸው ብለን አስበናቸው የነበሩ ተግባራትን ለመከወን ይህ የእፎይታ ጊዜ ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡

የተለመዱ እና ሊከሰቱ የሚችሉ ተግባራትን ሲያውቁ ልጆች ደህንነት ይሰማቸዋል፡፡ ሰለዚህ በየሳምንቱ በምናወጣቸው እቅዶች ላይ የልጆቹን እቅድ ከእኛ ጋር ማጣመር መዘንጋት የለብንም፡፡ ከቤትዎ ሆነዉ የቢሮ ስራ ሚሰሩ ከሆነ እርሶ ስራዎትን በሚሰሩበት ጊዜ በተመሳሳይ ሰዓት ልጆቹ ትምህርታቸውን እንዲያከናውኑ ማድረግ ውጤታማ ያደርገናል፡፡

 

እቅድ ማዘጋጀት-

የሁሉን አካታች የሆነ የእቅድ ቻርት ማዘጋጀት፡፡ በየሳምንቱ አዳዲስ የእቅድ ቻርቶችን ማዘጋጀት አዳዲስ ተግባራትን እንደአስፈላጊነቱ በየጊዜው ለመጨመር ይረዳል፡፡

 

2. ኢላማዎች ማዘጋጀት

ራስዎንና የምትወድዋቸውን ሰዎች በጣም የተጣበበ ፕሮግራምና ለመስራት የሚያዳግቱ ኢላማዎችን በመቅረጽ አታጨናንቇቸዉ፡፡ ራስን ለውድቀት አያዘጋጅ፡፡ትልልቆቹን ኢላማዎቸ ወደትንንሽ የሚሰሩ ተግባራት ይክፈሏቸው፡፡ ልጆቾዉን በትምህርት ቤት ስራዎች እንዲያተኩሩ ያግዟቸው፡፡

3. ቋሚ/ወጥነት ያለው/ ጊዜ ማበጀት

ጊዜያችንን በአግባቡ ለመጠቀም የሚያስችለንን እቅድ በማዘጋጀት የምንሰራቸውን ተግባራት በታቀደው ጊዜ መሰራቱን ክትትል ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ ስራዎቻችንን በትኩስ ጉልበት በጠዋት ማከናወን ውጤታማ እንድንሆን ከማድረግ በተጨማሪ ቀኑን ልንሰራቸው ያሰብናቸውን ተጨማሪ ተግባራት በመከወን ተጠቃሚ እንድንሆን ያደርገናል፡፡ህጻናት ልጆች ካሉን ከስራ ጋር የተያያዙ ተግባራትን እንቅልፍ በሚተኙበት ሰዓት ብንተገብር እንዲሁም የአካል እንቅስቃሴ የሚፈልጉትን ደግሞ ከእንቅልፋቸው ሲነሱ ለመከወን ማቀድ፡፡

 

4.ቤት ውስጥ የተለያዩ ተግባራትን ለመስራት የተለያዩ ቦታዎችን መምረጥ

በትልቅ ቪላ ይሁን አነስ ባለች በአንድ ክፍል ቤት ውስጥ የሚኖሩት ፣ የመኖሪያዎትን ቦታ የተለያዩየ ቀን ተግባራትን ለማከናወን ከፋፍሏቸው፡፡ ለምሳሌ አልጋዎን ለመተኛት እንዲሁም የመመገቢያ ጠረጴዛውን ለስራ መጠቀም፡፡

5. እረፍት መውሰድ

ራስን ዘና፣እድስ በማድረግ በአዲስ ጉልበት መሙላት አስፈላጊ ነዉ፡፡በየመሃሉ ትንንሽ እረፍቶችን መውሰድ ለአእምሯችን ጉልበት በመስጠት ውጤታማ ስራ እንድንሰራ ያደርገናል፡፡በየመሀሉ የምናደርጋቸውን እረፍቶች የተለያዩ ተግባራትን ለመከወን መጠቀም እንችላለን፣ለምሳሌ በቴክኖሎጂ( በስልክ ወይም እንደስካይፕ ያሉ ማህበራዊ ሚዲያዎችን) ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር ለመገናኘት መጠቀም እንችላለን፡፡

6. ለውጥን መከታተል

በየቀኑ እቅዶቻችንን ባስቀመጥነው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ማከናወናችንን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው፡፡ይህ በየቀኑ ራስን የመከታተል ቀላል ተግባር የስኬታማነት ስሜት እንዲሰማን ያደርገናል፡፡

7. ራስን መሸለም

 

 

በዚህ ቤት መቆያ ጊዜ ራስን መሸለም እራስን ለማበርታት ቁልፍ ነው፡፡

8. ዜና ለማዳመጥ የምናጠፋውን ጊዜ መወሰን

በተለያዩ ሚዲያዎች እና ማህበራዊ ድህረ ገጾች ኮቪድ-19 በተመለከተ እጅግ ብዙ መረጃዎች ይለቀቃሉ፡፡ ስለበሽታው መስፋፋት ወቅታዊ የሆኑ መረጃዎችን መከታተል አስፈላጊ ቢሆንም የምናገኛቸው መረጃዎች ከታማኝ ምንጮች መሆናቸውን ማረጋገጥ ይኖርብናል፡፡ የተሳሳቱ መረጃዎችን ለመቀነስ የአለም ጤና ድርጅት ስለወረርሽኙ የሚያወጣቸውን ሪፖርቶች እንዲሁም ሃላፊነት የተሳጣቸው የመንግስት ተቋማት ሪፖርቶችን እንድትከታተሉ እንመክራለን፡፡