ተጨማሪ ኮቪድ - 19

ቤት ውስጥ ራስን ለይቶ ማቆየት

ፍቺ

ለይቶ ማቆየት ማለት አንድ በበሽታ ከተጠቃ ሰው ጋር ተጋላጭነት የነበረው ሰውን ከሌለው (ከጤነኛው) መለየት ነው፡፡ ብዘውን ጊዜ ሰዎች በቫይረሱ መጠቃታቸውን አያውቁትም (ለምሳሌ ሲጓዙ ወይም ከህዝብ ጋር በጋራ ሲሆኑ) ወይም በበሽታው መጠቃታቸውን ሳያውቁና ምልክት ሳይታይባቸው በሽታው ይኖርባቸዋል፡፡

ለብቻ ማግለል ማለት አንድን ታማሚ ከጤነኛው ሰው መነጠል ነው፡፡ ራሳቸውን እያገለሉ ያሉ ሰዎች ቤት ውስጥ መቆየት ይኖርባቸዋል፡፡እነኚህ ሰዎች ቤት ውስጥ በሚቆዩበት ጊዜ በተቻለ መጠን በራሳቸው በሆነ አንድ ክፍል ውስጥ መሆን ይኖርባቸዋል ቢቻል ሽንት ቤትም ጭምር ቢለይ ይመረጣል፡፡

ምንጭ፡ ከበሽታ መከላከልና ቁጥጥር ባለስልጣን

በኮቪድ-19 የተጠቁ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመጣ ጊዜ ቀለል ያለ የበሽታ ምልክት የሚታይባቸው ሰዎች ራሳቸውን እንዲያገሉ ይጠበቃል፡፡ በብዙ መካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሀገሮች ራስን ማግለል ባለው አነስተኛ ሃብት፣የተጨናነቀ/የተፋፈገ የኑሮ ሁኔታና አነስተኛ መኖሪያ ቦታ ፈታኝ ያደርገዋል፡፡ ይህ መመሪያ ራስን እንዴት ማግለል እንዳለብን ከመጥቀሙ በተጨማሪ ትንሽ ሃብት ባለበት ሁኔታ ራስን ማግለልን እንዴት ማካሄድ እንዳለብን ይጠቁማል፡፡

ጥብቅ የራስን ለይቶ ማቆያ መመሪያ መከተል ያለበት ማን ነዉ?

የቫይረሱ ምልክት የሌለባቸዉ ነገር ግን ኮቪድ – 19 ከተያዘ ግለሰብ ግንኙነት የሚኖራቸዉ ሰዎች ናቸዉ፡፡

ትኩሳት ወይም ሳል ያለባቸዉ ግለሰቦች እና የልየታ ስራ በሚሰራዉ ቡድን በቫይረሱ የተጠቁ ሊሆኑ ይችላሉ ተብለዉ የተለዩ ግን ያልተመረመሩ ናቸዉ፡፡

የአዉሮፓ በሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማዕከል/ European Center for Disease Prevention and Control (ECDC) “contact person”ን ወይም ግንኙነት ያለዉ ቫይረሱ ከተያዘ ግለሰብ ጋር የምርመራ ናሙና ከመወሰዱ ሁለት ቀናት በፊት እስከ ናሙናዉ ከተወሰደ 14 ቀናት በኋላ ንክኪ ያለዉ በማለት ትርጓሜ ይሰጠዋል፡፡

እነደ የአዉሮፓ በሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማዕከል ሁለቱ አደገኛ ተጋላጭነቶችን እንደሚከተለዉ አስቀምጧቸዋል፡-

  1. በቫይረሱ ከተያዘ ግለሰብ ጋር በ2 ሜትር ዉስጥ ፊት ለፊት ለ15 ደቂቃ እና ከዚያ በላይ ቆይታ የነበረዉ ግለሰብ
  2. በቫይረሱ ከተያዘ ግለሰብ ጋር ዝግ በሆነ ክፍል ዉስጥ የነበረ (ምሳሌ፡- የመማሪያ ክፍል፤ የስብሰባ ክፍል፣ የሆስፒታል ወረፋ መጠበቂያ ክፍል/ቦታወ.ዘ.ተ…)

ተጨማሪ የተጋላጭነት መንገዶችን የአዉሮፓ በሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማዕከል በቫይረሱ ከተጠቁ ግለሰቦች ጋር ንክኪ ያላቸዉን ማህበረሰቦች ማስተዳደሪያ አስመልክቶ ያወጣዉን ሪፖርት መመልከት ይቻላል፡፡

እንዴት ራስን ለይቶ ማቆየት ይቻላል

የማህበረሰብ ስርጭትን ለመከላከል

ራስን በቤት ዉስጥ ለይቶ ማቆየት

መሰረታዊ የሆኑ ዕቃዎችን (ምግብ እና መድሀኒት) የምትፈልጉ ከሆነ ሌላ ሰዉ እንዲያመጣላችሁ መጠየቅ፡፡ እንዲሁም ሲቀበሉ ቢያንስ 2 ሜትር ርቀት በመካከላችሁ እንዲኖር እና በበር ላይ አስቀምጠዉ እንዲሄዱ በማድረግ እቃዉን መዉሰድ ይችላሉ፡፡

አስፈላጊዉን የመከላከያ አልባሳት የለበሱ የሚንከባከብዎት ሰዎች ካልሆኑ በቀር የሚጎበኝ ሰዉ ሊኖር አይገባም:

እንክብካቤ የሚያደርግልዎት ግለሰብ መመሪያዉን ተከትለዉ መስራት ሲኖርባቸዉ በቤት ዉስጥ የሚኖሩ አባላትን እንዳያጋልጡ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ እንክብካቤ የሚያደርገዉ ግለሰብ ወደራሱ ቤተሰቦች እንዳያስተላልፍም አስፈላጊዉን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

የበሽታዉን ስርጭት በአንድ ቤት ከሚኖሩ አባላት መከላከል

አለም ዓቀፍ የጤና ድርጅት (WHO) በቫይረሱ የሚጠቃ ማንኛዉም ግለሰብ ራሱን ከሌሎች ሰዎች እና የቤት እንስሳቶች በቂ አየር በሚገባበት ክፍል መለየት እንዳለበት ይመክራል፤ ከተቻለ የተለየ መጸዳጃ ክፍል ቢጠቀም ይመረጣል፡፡

ከሌሎች ሰዎች ጋር ክፍል መጋራት አስገዳጅ ከሆነ፤ ሁሉም ክፍሎች በቂ አየር እንዲያገኙ ማድረግ እና በቤት ዉስጥ ከሚኖሩ ሰዎች ጋር በተለይም ተጋላጭነታቸዉ ከፍተኛ ከሆኑ ግለሰቦች በ2 ሜትር (ሶስት እርምጃ) ርቀት ልዩነት ሊኖር ይገባል፡፡

የተለየ አንሶላ፤ ፎጣ እና የመገልገያ ዕቃዎች ያዘጋጁ እነዚህንም ከተጠቀሙ በኋላ በሳሙናና ዉኃ በማጠብ ሌሎች የቤተሰቡ አባላት እንዳይጠቀሙባቸዉ ያድርጉ፡፡ ይህንን በራስዎ ማድረግ ካልቻሉ የሚንከባከብዎት ግለሰብ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ለብሶ እንዲያጥብልዎት እና ሲጨርሱ እጃቸዉን እንዲታጠቡ ያድርጉ፡፡

በጋራ በጠቀሚያ መጸዳጃ ቤቶችን እና በብዛት የሚነኩ ቦታዎችን በደንብ ማጽዳት፤ እና ከተቻለ የጋራ መገልገያ እና በብዛት የሚነኩ ዕቃዎችን የሚቆጣጠር፡፡ አንድ ሰዉ መመደብ እንደ በሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማዕከል፣ በብዛት የሚነኩ ዕቃዎች የሚላችዉ፡ ስልኮችን፤የቴሌቪዥን መቆጣጠሪያ፤ እንግዳ መቀበያዎች ፤ የጠሬጴዛ የላይኛዉ ክፍል፤ የበር እጀታዎች፣ የባኞ ቤት ዕቃዎች፤ የመጸዳጃ ቤቶች እና የመኝታ ክፍል ጠረጴዛዎች ናቸዉ፡፡

ከሌሎች የቤተሰቡ አባላት ጋር ሲሆኑ ሁልጊዜም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ይጠቀሙ፡፡

ከእርስዎ የሰዉነት ፈሳሽ ጋር ግንኙነት ያላቸዉ መልሰዉ ጥቅም ላይ የማይዉሉ እቃዎች ካሉ ሌሎች ሰዎች በማይደርሱበት ቦታ ክዳን ባለዉ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ይጣሉ፡፡

ከለይቶ ማቆያ መቼ ይዉጡ

እርስዎ ራስዎን ለይተዉ ያቆዩት የኮቪድ-19 መሰል ምልክቶች በማሳየትዎ ከሆነ የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ራስዎን ለይተዉ ካቆዩበት ቦታ መዉጣት ይችላሉ፡

    • ህመም ተሰምቶዎት ራስዎን ከለዩ 7 ቀናት ካለፈ
    • ትኩሳት ከሌለዎት፡ ትኩሳት ካለዎት ትኩሳቱ እስኪጠፋ ድረስ በለይቶ ማቆያዉ ይቆዩ፡፡ ኢንፌክሽኑ ጠፍቶም ሳል ሊኖርዎት ይችላል፡:

በቫይረሱ ከተጠቃ ግለሰብ ጋር ንክኪ ስላለዎት ራስዎን ለይተዉ እያቆዩ ከሆነ ከእርስዎ ጋር ንክኪ የነበረዉ የቫይረሱ ተጠቂ ምልክት ማሳየት ከጀመረበት 14 ቀናት በኋላ ራስዎን ለይቶ ማቆየትዎን ማጠናቀቅ ይችላሉ፡፡