የ ኮቪድ - 19 የመማሪያ እና የማስረጃ መገልገያዎች

እነዚህ የመረጃ ምንጮች ከብዙ ሰዎች የተስብስብ ሥራዎች ፣ መረጃዎችና አስተያየቶች ሲሆኑ ለ “STAR Fellowship” ፕሮግራም የተጠናከረ  የመረጃ ስብስቦችን ያካትታሉ። ሌሎች ጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ ብለው የሚያምኑት ተጨማሪ የመረጃ ምንጮች ካሉዎት እባክዎን ወደ info@iifphc.org ይላኩ

የአለም ጤና ድርጅት

  1. ከ ኮቪድ-19 እራስዎን እንዴት እንደሚከላከሉ?
    • ስለ ኮቪድ-19 የበለጠ ለማወቅ እና እራስዎን ከዚህ ለመከላከል እንዴት እንደሚችሉ መረጃ ለማግኘት ይህንን አጭር መልክታዊ ቪዲዮ ይመልከቱ፡፡

  2. #ንፁህእጅ ፉክክር

    • ኮራና ቫይረስን ለመከላከል በጣም ውጤታማ ከሆኑ መሳሪያዎች መካከል አንዱ ትሑት የሆነው የሳሙና አሞሌ ነው፡፡

      በንጹህ እጆች በጋራ ኮቪድ-19ን እንዋጋ፡፡

  3. ኮቪድ-19 በምን መልኩ ነዉ  ሚሰራጨዉ?

    • የምእራብ ፓሲፊክ የአለም ጤና ድርጅት የክልል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ / ር Takeshi Kasai ኮቪድ-19 እንዴትእንደሚሰራጭ እና እራስዎን እና ቤተሰቦን ከዚህ ቫይረስ እንዴት መጠበቅ እንደሚችሉ ይናገራሉ፡፡

  4. ስለ ኮቪድ-19 ያለ የተሳሳቱ መረጃዎች ስርጭትን መቅረፍ፡፡

    • የበሽታ ወረርሽኝ በሚከሰትበት በማንኛውም ጊዜ የተሳሳተ መረጃ እና ወሬ ከቫይረሱ ራሱ በፍጥነት ሊሰራጭ ይችላል ይህም ከቫይረሱ እኩል አደገኛ ሊሆን ይችላል።

      እራስዎን እና ቤተሰቦዎን ከኮቪድ-19 ለመጠበቅ ሁል ጊዜ እውነታውን ማወቅዎን ያረጋግጡ።

  5. ከ ኮቪድ-19 ጋር የተቆራኘ ወንዴ ዋጦን መቅረፍ፡፡

    • ቃላት ታላቅ ተጽዕኖ አላቸዉ፡፡ ወንዴ ዋጦ ሰዎችን በማግለል ፣ የጤና እንክብካቤ ከማግኘት ይገድባቸዋል እንዲሁም ጤናማ ሥነምግባርን ከመይዝ ይከለክላቸዋል፡፡ከ ኮቪድ-19 ጋር የተጎዳኘውን ነቀፋ ለማስወገድ እንዴት ማገዝ እንደሚችሉ የበለጠ ለማወቅ ይህንን አጭር ቪዲዮ ይመልከቱ።

  6. ስለ ኮቪድ-19 ምን ያውቃሉ?
    • በጤና ላይ ድንገተኛ አደጋን እያስከተለ ስላለዉ ኮሮና ቫይረስ ምን ያውቃሉ?

  7. ትኩሳትና ሳል ካለው ማንኛውም ሰው ጋር የቀረበ ግንኙነት እንዳይኖረዎ ለምን ይመከራል?

    • ከአዲሱ ኮሮና ቫይረስ እራስዎን ለመጠበቅ ብዙ መንገዶች አሉ፡፡ከሚመከሩት እርምጃዎች ውስጥ አንዱ ትኩሳት እና ሳል ካለው ማንኛውም ሰው ጋር የቀረበ ግንኙነት እንዳይኖር ማድረግ ነው፡፡

  8. ከአዲሱ ኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ጭምብሎች መቼ እና እንዴት ጥቅም ላይ መዋል አለባቸው?

    • እንደ ትኩሳት ፣ ሳል ፣ ወይም ቀጭን ንፍጥ የመሳሰሉት የመተንፈሻ አካላት በሽታ ምልክቶች ከሌሉዎት የህክምና ጭምብል ማድረግ የለብዎትም። ጭምብል ብቻውን ሲገለገሉ የውሸት የሙሉ በሙሉ የመከላከል ስሜት ይሰጡዎታል እናም በትክክል ባልተጠቀምንበት ጊዜም የኢንፌክሽን ምንጭ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

  9. በአዲሱ በኮሮና ቫይረስ በሽታ እንዳያዙ ሰዎች እራሳቸውን እና ሌሎችን ለመጠበቅ ምን ማድረግ ይችላሉ?
    • ከአዲሱ ኮሮና ቫይረስ በሽታ እራስዎን ለመከላከል ሊወስድዋቸዉ የሚችሏቸው በርካታ እርምጃዎች አሉ፡፡የአለም ጤና ድርጅት ባለሙያዎች የሚመከሩ ምክሮችን ለማዎቅ ይህንን አጭር ቪዲዮ ይመልከቱ፡፡

  10. አዲሱ ኮሮና ቫይረስ በበሽታው በተያዙ ሰዎች ላይ ምን አይነት የጤና ተጽዕኖ ያመጣል?

    • እንደሌሎች የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቁ በሽታዎች ሁሉ ፣ የ 2019 ኮሮና ቫይረስ ኢንፌክሽን የንፍጥ መፍሰስ ፣ የጉሮሮ መቁሰል ፣ ጉንፋን እና ትኩሳትን ጨምሮ መለስተኛ ምልክቶችን ሊያስከትል ይችላል። ለአንዳንድ ሰዎች ይበልጥ ከባድ ሊሆን ይችላል ፣ እና በጣም አልፎ አልፎ ፣ ለሞት ሊዳርግ ይችላል፡፡ 

  11. የቫይረሱን ስርጭትን ለማስቀረት የሚረዱ ሰባት እርምጃዎች።

    • የ #ኮቪድ-19# ወረርሽኝ መደበኛ መግለጫ እራስዎን እና ቤተሰቦዉን ለመጠበቅ እነዚህን ቀላልእርምጃዎች መውሰድ እና መለወጥ ያለብዎትን እውነታ አይለውጠውም፡፡

 

የአፍሪካ ክልል አ.ጤ.ድ

  1. በቲፒ ታፕ ሲስተም እጅ አጠባ 
  • ኮቪድ-19 እንዳይዛመት ለመከላከል እጅን መታጠብ ከመንገዶች ውስጥ አንዱ እና ዋነኛዉ ነዉ፡፡ ግን ሁሉም ሰው ሁል ጊዜ የውሃ ፍሰት የለውም። ነገር ግን በአለማችን ላይ የዉሀ አገልግሎት እንደልብ ማይገኝባቸዉ አካባቢዎች በብዛት አሉ። ይህ የቲፒ ታፕ ሲስተም የዉሀ አገልግሎት በአግባቡ ለሕብረተሰቡ በማይደርስበት አካባቢዎች በቀላል እና በዉሀ በማያባክን እንዲሁም ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ እጅን ለመታጠብ የሚያስችል ሲስተም ነዉ።

የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከያ ማዕከል

  1. የግል መከላከያ መሣሪያዎችን (PPE) በአስተማማኝ ሁኔታ እንዴት መልበስ?

    • ይህ ቪዲዮ የሚያሲያየዉ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከያ ማዕከል የግል መከላከያ መሣሪያዎችን የጤና ባለሞያዎች በአግባቡ እንዴት መልበስ እንዳለባቸዉ የሰጡትን መረጃ ነዉ።
  2. የግል መከላከያ መሳሪያዎችን በአግባቡ እንዴት ማውጣት እንዳለብን። 
    • ይህ ቪዲዮ የሚያሲያየዉ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከያ ማዕከል የግል መከላከያ መሣሪያዎችን የጤና ባለሞያዎች በአግባቡ እንዴት ማዉለቅ እንዳለባቸዉ የሰጡትን መረጃ ነዉ።
  3. ለከባድ ህመም የመጋለፅ ዕድሎ ከፍተኛ ነዉን። 
    • በዕድሜ የገፉና በማንኛውም ዕድሜ ላይ ያሉ የከባድ ጤና እክሎች ያሉባቸው ከ ኮቪድ-19 ለሚመጡ ከባድ ችግሮች ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡

  4. በቤት ውስጥ ኮቪድ-19ን ለመቆጣጠረ ማድረግ የሚችሏቸው 10 ነገሮች።

    • በ ኮቪድ-19 በሽታ የታመሙ ከሆነ ወይም በቫይረስ እንደተያዙ የሚያምኑ ከሆነ ፣ በቤትዎ እና በማህበረሰብዎ ውስጥ ወደ ሰዎች እንዳይሰራጭ ለመከላከል ከዚህ በታች ያሉትን መረጃዎች ይከተሉ ፡፡

  5. ኮቪድ-19ን ለመከላከል እነዚህን 6 እርምጃዎች ይከተሉ።

    • በ ኮቪድ-19 የመታመም እድለዎን ለመቀነስ የተለያዩ እርምጃዎችን ይውሰዱ፡፡ ማድረግ የሚችሉት አንዳንድ ነገሮች እነሆ፡፡

  6. አዛውንት አዋቂዎች ማወቅ የሚገባቸው ነገሮች። 
    • የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል የተላላፊ በሽታዎች ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ጄይ ሾለር ፣ አዛውንቶችን ከ ኮቪድ-19 ለመከላከል የሚረዱ የመከላከያ እርምጃዎችን ገልፀዋል፡፡

  7. የ2019 የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክቶች

    • ይህ ቪዲዮ የኮሮና ቫይረስ ምልክቶችን እና ምልክቶቹ ከታዩ ምን ማድረግ እንዳለበት ያሳያል ፡፡
  8. ስለ እጅ መታጠብ ማወቅ ያለብዎት ነገሮች። 
    • ይህ ቪዲዮ ስለ በእጅ መታጠብ እና የእጅ ማፅጃ አስፈላጊነትን ዙሪያ ጥያቄዎችን ይመልሳል ፡፡
  9.  የፊት ሽፋን እራስዎ በቤቶ እንዴት እንደሚሠሩ 
    • የጄኔራል ቀዶ ጥገና ዶክተር ጀሮም አዳምስ የራስዎን የፊት ሽፋን በቀላሉ እንዴት መስራት እንደሚቻል ይጋራሉ፡፡
  10. ኮቪድ-19 በተለያዩ ገጽታዎችና በአየር ላይ ሊቆይ ይችላል?

    • የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል የኮቪድ-19 ምላሽ ዋና የሕክምና ኦፊሰር የሆኑት ዶክተር ጆን ብሩክስ ስለ  ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ቁልፍ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል፡፡

  11. ኮቪድ-19 እንዴት ይተላለፋል?

    • የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል ዶክተር ዶ / ር ናንሲ ሜንደርኒየር ኮሮና ቫይረስን ጨምሮ የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቁ ቫይረሶችን ስርጭት ለመከላከል ዕለታዊ የመከላከያ እርምጃዎችን ይመክራሉ ፡፡

  12. እራሴን ከኮቪድ-19 እንዴት መጠበቅ እችላለሁ?

    • ከኮቪድ-19 መከላከልን በተመለከተ መረጃ

  13. የማህበራዊ ርቀት

    • ከሌሎች ጋር የፊት ለፊት መገናኘትን መገደብ የኮሮና ቫይረስ በሽታ ስርጭትን ለመቀነስ ዋነኛዉ መንገድ ነው ፡፡
  14. ስለ ኮቪድ-19  ለ20 ጥያቄዎች መልስ ተሰጠ

    • በዚህ በየበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል የተካሄደዉ ልዩ ምናባዊ ስብሰባ ላይ ዶ / ር ጄይ በትለር የወረርሽኙ ወቅታዊ ሁኔታ ፣ ለወረርሽኙ ምላሽ ለመስጠት የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል  ምን እያደረገ እንደሆነና ፣ አጋሮች ፣ ድርጅቶች እና ህዝቡ እንዴት መርዳት እንደሚችሉ አካፍለዋል፡፡

  15. ኮቪድ-19 ከያዘን ወደ ሆሰፒታል ለህክምና መሄድ የሚኖርብን መቼ ነዉ?

    • ከባድ ወይም የሚያሳሳስብ የጤና ምልክቶችን እያጋጠሙዎት ከሆነ ለህክምና ወደ ሆሰፒታል መሄድ እንዳለቦት የበለጠ ይረዱ።

  16. እራስዎን ይጠብቁ

    1. የኮሮና ቫይረስ በሽታ እንዳይሰራጭ ራስዎን ለመከላከል ሊወስድዋቸው ስለሚችሏቸው እርምጃዎች ሰዎችን ለማሳወቅ የተቋቋሙ ማስታወቂያዎች፡፡ አንድ ላይ በመሆን ፣ ስርጭቱን ማስቆም እንችላለን ፡፡

  17. Ibuprofen ኮቪድ-19ን ሊያባብሰው ይችላልን?

    • የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል ዋና የሕክምና ኦፊሰር የሆኑት ዶክተር ጆን ብሩክ ስለ ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ቁልፍ ጥያቄ ምላሽ ይሰጣሉ፡፡

  18. ጭንቀትን እና ውጥረትን መቆጣጠር

    • በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ጭንቀትንና ዉጥረትን እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል ምክሮችን ይጋራል፡፡

  19. በኮቪድ-19 ለተያዘ ሰው እንክብካቤ መስጠት

    • የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል በኮቪድ-19 በቤት ውስጥ በኮቪድ-19 ለተያዘ ሰው እንክብካቤን መስጠት ላይ ምክሮችን ይጋራል፡፡

  20. ስርጭቱን ለመቀነስ የበኩሎቱን ያድርጉ፡፡

    • የኮቪድ-19 ስርጭትን ለማስቀረት ሁሉም ሰው የበኩሉን ማድረግ ይችላል።

  21. ወላጆች ልጆችን ይደግፉ

    • የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ወላጆች እና አሳዳጊዎች ልጆችን እና ታዳጊዎችን እንዴት መደገፍ እንደሚችሉ ምክሮችን ይሰጣል ፡፡

የአውሮፓ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል

  1. ስለ ኮሮና ምን እናውቃለን?

     

    • የኮቪድ-19 በሽታን ስለሚያስከትለው SARS-CoV2 ቫይረስ ምን እናውቃለን? እንዴት ይተላለፋል? በበሽታው የመያዝ እድልን ለመቀነስ አንድ ሰው ሊወስዳቸው የሚገቡ እርምጃዎች ምንድናቸው? የቤት እንስሳት ጋር መነካካት ጉዳትን ያስከትላል።

  2. አካላዊ ርቀትን መጠበቅ።

  3. እጅዎን በአግባቡ እንዴት መታጠብ እንዳለቦ ያውቃሉ?

የተባበሩት መንግሥታት የህፃናት መርጃ ድርጅት /UNICEF/

  1. ስለ ኮሮና ቫይረስ ከልጆችዎ ጋር በምን መልኩ መወያይት እንደሚችሉ

    • የ #ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለህፃናት ጭንቀት እና ግራ መጋባትን ሊያስከትል ይችላል። ችግሩን እንዲቋቋሙ ለማገዝ አንዳንድ ቀላል እርምጃዎች እነሆ።

  2. የኮኖና ቫይረስ ወረርሽኝ

    • ኮሮና ቫይረስ በተስፋፋበት ቁጥር ወላጆች ማወቅ የሚያስፈልጋቸው ስድስት ነገሮች።

የተባበሩት መንግሥታት የህፃናት መርጃ ድርጅት /UNICEF ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ

  1. ራስዎን ከኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ይህንን መልእክት በመተግበር ጥንቃቄ ያድርጉ! ለሌሎችምያጋሩ!       

ሜዮ ክሊኒክ /Mayo Clinic/

  1. የኮቪድ-19 ምልክቶች እና ስለ አሰረጫጨቱ መረጃ    

  2. የኮቪድ-19 ባለሙያዎች ማህበራዊ ርቀትን ሰዎች በሚጠብቁበት ጊዜ ማድረግ ያለባቸዉንና የሌለባቸዉን ነገሮች ዙሪያ ለተጠየቁት ጥያቄ ምላሽ ይሰጣሉ።

ሃርቫርድ/Harvard/

  1. ኮሮና ቫይረስን መቋቋም ላይ አራት ምናባዊ ስብሰባዎች


    • የጭንቀት ሚና

    • የአንጎል እርጋታን

    • ኃይል መሰብሰብና ከዉጪዉ ዓለም ጋር በርቀት መገናኘትን መቀጠል

    • ሀሳቦችን መመርመር

      • የዕለት ተዕለት ውጥረትን ፣ ጭንቀትንና የተለያዩ ስሜቶችን መቋቋም

  2. ኮቪድ-19 : ከዚህ በህዋላ ወዴት እንሄዳለን?


    • በሀርቫርድ ቲ.ኤች ቻን /Harvard T.H. Chan/ የማሕበራዊ ጤና ትምህርት ቤት እና የኒው ኢንግላንድ የሕክምና መጽሔትየቀረበ ምናባዊ ሲምፖዚየም ላይ በኮቪድ-19 ዙሪያ ስለሚቀጥሉት የጋራ እርምጃዎቻችን ከጤና መሪዎች ጋር ወቅታዊ እና አስፈላጊ ውይይት አድርገዋል። ወሳኝ አቅርቦቶችን ማስቀመጥ ፣ የሕክምና እና የክትባት ምንጮችን ፣የሕብረተሰብን እንቅስቃሴ መጀመርን አሰመልክቶ  ባለሙያዎች እንዴት በተሻለ ሁኔታ መቀጠል እንደሚችሉ ዳስሰዋል፡፡

  3. በአፍሪካ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት እና የጤና ስርዓት በሚዳከምበት ጊዜ የአእምሮ ጤናን ተኩረት መስጠት

     
    • በዚህ መድረክ ላይ ፣ በደቡብ አፍሪካ ከሚገኘው የኪዙሉ-ናታል ዩኒቨርሲቲ /University of KwaZulu-Natal in South Africa/ ዶ / ር ካረንታን ኮየንና /Karestan Koenen/ ዶ / ር ቢዙ ገላዬና /Bizu Gelaye/ ዶ / ር ቦንጋ ቺሊዛን /Bonga Chiliza/ እና በኬንያ ውስጥ ከሚገኙት የሞኢ /Moi/ ማስተማር እና ሪፈራል ሆስፒታል በአፍሪካ ከ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተዛመደ የአእምሮ ጤንነት ጉዳዮች ላይ ዉይይት አድርገዋል። ፓናልስቶቹ የአፍሪካ የጤና አጠባበቅ ስርዓት እና የአእምሮ ጤና ባለሙያዎች በአሰቃቂ ሁኔታ እየጨመረ ላለዉ የኮቪድ-19 ታማሚዎች ቁጥር እንዴት እየተዘጋጁ እንዳሉ ይናገራሉ።

  4. ስለ ኮሮና ቫይረስ ዎረርሽኝ ዛሬ ምን እናዉቃለን

     
    • የዓለም ጤና ድርጅት ኮቪድ-19ን ወረርሽኝ ካወጀ ከአንድ ወር በኋላ የበሽታው ወረርሽኝ ባለሙያ የሆኑት ካሮላይን በክ /Caroline Buckee/  የምላሹን ሁኔታ ገምግመዋል ፡፡ በflattening the curve የቫይረሱ ስርጭትን ለማስቆም በሚደረገዉ ጥርት የት ደርሰናል? ስለ ቫይረሱ ፣ ክትባቶች እና ህክምናዎች ያለን ወቅታዊ ግንዛቤ ምን ይመስላል? ከማህበራዊ ርቀቶችን የመጠበቅ እርምጃዎች ምን ተጽዕኖዎች ተገኝተዋል? እና ከዚያ በኋላ ምን መጠበቅ እንችላለን?

  5. ውጥረትን  መቆጣጠር –  የኮቪድ-19ን ወረርሽኝን ለመቅርፍ የሚረዱ ስትራቴጂዎች

     
    • በዚህ መድረክ ላይ ፣ ዶ / ር አማንቲያ አሜቴጅ /Amantia Ametaj/ እና ዶ / ር ክሪስቲና ኮርት / Kristina Korte/ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ቲያይዘዉ የሚነሱትን ​​ደስ የማይሉ ስሜቶችን ለመቆጣጠርጋር የሚያስችሉ መንገዶችን ይወያያሉ፡፡ምቾትን የሚነሱ  ስሜቶች ለምን እንደሚከሰቱ ፣ ምን እንደሚሰማዎት በተሻለ እንዴት እንደሚረዱ እና ለጊዜው እራስዎን ለማዳን የሚረዱ መንገዶችን በአጭሩ ይገምግማሉ፡፡ከዚህ ንግግር ቀጥሎ ሁሉም ሰው በቤት ውስጥ ሊሞክረው የሚችሏቸው አንዳንድ እንቅስቃሴዎችን ይዳስሳሉ።

  6. ሐዘኔታ እንዴት ሊረዳን ይችላል?

     
    • በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት እጦትን መገንዘብ እና መላመድ 

      • በዚህ ምናባዊ ውይይት ላይ ዶ / ር ካርስተን ኮነን /Karestan Koenen/ ዶ / ር ካቲ ሺርና /Kathy Shear/ ዶ / ር ክሪስቲ ዴንክላና /Christy Denckla/ አርቻና ባሱ በመሆን ከ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር ተዛምደዉ የሚከሰቱትን እጦቶችን መላመድ ስለ ሚችልበት መንገድ ላይ ውይይት አድርገዋል። አቀራ ቢዎቹ ሀዘን ምን እንደሚመስል ፣ በሀዘን ላይ ሲሆነ ምን አይነት ስሜት ሊሰማዎት እንደሚችል፣ እና ከወረርሽኑ ጋር የተዛመዱትን እጦቶች ለመቋቋም የሚያስችሉ መንገዶችን በአጭሩ ገልጸዋል።

           

ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ /Johns Hopkins University/

 

  1. ኮቪድ-19 – ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ /Johns Hopkins University/ ባለሞያዎች ስለ ወረርሽኝ ምላሽ ፣ ማህበራዊ ርቀትን መከተል እና ስለሌሎች ጉዳዮች ተወያይተዋል፡፡  

     
    • ኮቪድ-19 ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ መሆኑ ታዉጅዋል፡፡ ንግዶች ተዘግተዋል ፣ የትምህርት ቤት ክፍሎችም ተዘግተዋል፣ የዓለም ኢኮኖሚ በከፋ መልኩ ተጎድትዋል። በዚህ ጊዜ እዉነተኛ የሆኑ መረጃዎችን ማስተላለፍ እና ሳይንሳዊ ማስረጃዎች ለዚ ሁሉ መፍትሄ ያገኛሉ በሎ ተስፋ ማድረግ ወሳኝ ነዉ። ምን አይነት ተግባሮች ናቸዉ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር ዉጤታማ የሆኑት? ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ በእዉነቱ ለዉጥ ያመጣል? ከዚህ ወረርሽኝ በዕለት ተዕለት ሕይወታችን እንዴት መጠንቀቅ እንዳለብን ምን ተምረናል?

  2. ኮቪድ-19 – ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ /Johns Hopkins University/ ባለሞያዎች ስለ ወረርሽኙ ተወያይተዋል፡፡

     
    • በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ የህብረተሰቡ ስርጭት በተመዘገበበት እና የአለም ጤና ድርጅት የአደጋ ስጋት ምዘናውን ወደ “በጣም ከፍተኛ” ባሳደገበት ዎቅት ይህንን ዓለም አቀፍ የጤና ችግር ዙሪያ ከጆንስ ሆፕኪንስ ብሉበርግ የህዝብ ጤና ትምህርት ቤት /Johns Hopkins Bloomberg School of Public Health/ የተወጣጡ ምሁራን የ 30 ደቂቃ ድር ጣቢያ ላይ ይመካከራሉ።
    • ፓናሊስቶቹ ዶ / ር ጄኒፈር ኑዙ /Dr. Jennifer Nuzzo/ ዶ / ር ታራ ከርክ ሼል /Tara Kirk Sell/ ከጆንስ ሆፕኪንስ የጤና የደህንነት ማዐከል /Johns Hopkins Center for Health Security/ እና ሎረን ሳዎር /Lauren Sauer/ ከጆንስ ሆፕኪንስ የወሳኝ ክስተት ዝግጅት እና ምላሽ ቢሮ /Johns Hopkins Office of Critical Event Preparedness and Response/ ያካትታል።
    • ኤክስፐርቶቹ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ /Donald Trump/ በጠቀስዋቸዉ የዓለም ጤና ደህንነት መረጃ ጠቋሚ ግኝቶች ስለ ማህበረሰብ ስርጭት ማወቅ ያለብን ነገሮች ዙሪያና ከተሳሳተ መረጃ እራሳችንን እንዴትመጠበቅ እንዳለብን ተወያይተዋል። በተጨማሪ ለተመልካቾች ጥያቄ መልስ በተጨማሪ ለተመልካቾች ጥያቄ መልስ ሰጥተዋል።
  3. ኮቪድ-19 – የበሽታውን ስርጭት እንዴት መከላከል እንደሚቻል

     
    • ለ #ኮሮናቫይረስ መስፋፋት ዝግጁ መሆንና ለመከላከል ግለሰቦች እና ተቋማት ምን ማድረግ ይችላሉ?

      በ እ.ኤ.አ. የካቲት 5 ቀን 2019 ከጆን ሆፕኪንስ ለጤና ደህንነት ጥበቃ እና ወሳኝ ክስተት ዝግጅት እና ምላሽ ማእከል የመጡ ባለሞያዎች በ #2019nCoV ወረርሽኝ ላይ ሰፊ ውይይት አካሂደዋል፡፡

      .

ጆንስ ሆፕኪንስ ሕክምና ማዕከል /Johns Hopkins Medicine

  1. ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምንድነው?  

       
    • የዓለም ጤና ድርጅት በ እ.ኤ.አ. ጥር 2020 አዲሱ የ #ካሮናቫይረስ በሽታን (ኮቪድ-19) በዓለም አቀፍ ደረጃ ወረርሽኝ መሆኑን ይፋ አደረገ፡፡ ከዚህን ጊዜ ጀምሮ የጆንስ ሆፕኪንስ ሕክምና ማዕከል ባለሙያዎች የቫይረሱ ስርጭትን በቅርብ እየተከታተሉ እና በሽታው ምን እንደ ሆነ እና ስርጭቱን ለመከላከል የሚረዱ ጠቃሚ መረጃዎችን ይሰጣሉ፡፡

  2. የ ኮቪድ-19 ኤ.ቢ.ሲ.ዎች

     
    • የ ኮቪድ-19 ተፅእኖን ለመቀነስ ሁላችንም አብረን በምስንሰራበት ጊዜ ብዙ መረጃዎችን እናነባለን እነዚህም መረጃዎች አንድ አንድ ጊዜ  የሚችሉ አዳዲስ ቃላትን በመጠቀም ግራ ሊያስገቡን ይችላሉ። እዚህ ድህረገፅ ላያ ሊያነብዋቸዉ ስለሚችሏቸው አንዳንድ ቃላት አጠቃላይ ትርጉም ያገኛሉ። 

  3. ልጆች እና ኮቪድ-19

     
    • በኮቪድ-19 አማካኝነት ልጆቻችን ላይ የተከሰተዉን ጭንቀት እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል ፤ ልጆች ከግዋደኞቻቸዉ ጋር መጫዎት መቻላቸዉን ፤ አያቶቻችን በበሽታው እንዳያዙ ማድረግ ያለብን ጥንቃቄዎች ምን ይመስላሉ ፤ በኮቪድ-19 የተያዘች አንድ እናት ጡት ማጥባት መቻልዋን ፤ የመሳሰሉት በኮቪድ-19 እና በቤተሰብ ዙሪያ ላሉ ጥያቄዎች

      የጆንስ ሆፕኪንስ የልጆች ማዕከል /Johns Hopkins Children’s Center/ የሕፃናት ሐኪም ዶ / ር ሬቾል ቶርተን /Rachel Thornton/ ለነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ ሰተዋል።

  4. ህመም ቢሰማኝ ምን ማድረግ አለብኝ?

    1. በኮቪድ-19 የተያዙ ከመሰሎት የእርስዎን ጤና እና የሌሎችን ጤና ለመጠበቅ እነዚህን እርምጃዎች ይከተሉ ።