ኮቪድ - 19 ላይ ተጨማሪ ገጾች

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

ከኮቪድ - 19 ጋር ተያያዥ የሆኑ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ዓለማችን እንድሁም ሀገራችን በተለያየ ጊዜ በወረርሽኝ መልክ የሚነሱ በሽታዎችን አስተናግደዋል፡፡ ለምሳሌ በተለምዶ የህዳር በሽታ (Spanish flu) የሚባለዉ ከእስያ ሀገራት ተነስቶ ዓለም ላይ ሰፊ ህዝብ የጨረሰ ነዉ፡፡ አንዳንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከ 50,000,000 -100,000,000 ህዝብ እንዳለቀ ነዉ፤ እንዲሁም የዓለም ፖለቲከኞችና  ትላልቅ ሰዎች ጭምር ያለቁበት ነዉ፡፡ ሌሎች ብዙ ቫይረሶች ለምሳሌ፤ እንደነ SARS, MERS-COV መዉሰድ እንችላለን ብዙ ህዝብ የጨረሱ ወረርሽኞች፡፡ ኮቪድ-19 ለየት የሚያረገዉ፤ በፍጥነት መዛመቱ፤ በአጭር ጊዜ ብዙ ቦታ ማዳረሱ፤ ለምሳሌ ባሁኑ ጊዜ ከ85% የዓለም ማህበረሰብ በዚህ ጉዳይ ዉስጥ ነዉ፤ በአፍሪካ ሁሉም ሀገራት በሚባል ደረጃ ተበክለዋል፤ አንዳንድ ሀገራት እስከ 7% ሰዎች እየሞቱ ናቸዉ፡፡ በተጨማረም በኢኮኖሚና በማህበራዊና በፖለቲካ ላይ የሚያሳድረዉ ጫና ኮሮና ቫይረስ በሽታን ለየት ያደርጋል፡፡

የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቁ በሽታዎች የመተላለፍ ዕድላቸዉ በጣም ከፍተኛ ነዉ፤ የቫይረሱ ባህሪ ሲያስል፤ ሲያስነጥስ በሚወጡ እርጥበታማ ትንፋሽ አማካይነት በመሆኑ እጅግ ፈጣን ነዉ፡፡ በተጨማሪም አንድ ሰዉ በቫይረሱ ከተጠቃበት ጊዜ ጀምሮ በአማካይ ከ 5 – 6 ቀናት ዉስጥ ምልክት ማሳየት ይጀምራል ይህም በጣም አጭር ጊዜ ነዉ፡፤ አንዳንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ሰዎች ምልክት ከማሳየታቸዉ ከ 1 – 2 ቀናት በፊት ማስተላለፍ ይችላሉ፤ በተጨማሪም 80% የሚሆኑ ሰዎች ምልክት አያሳዩም ወይም እንደ ተራ ጉንፋን ነዉ የሚታመሙት፤ ስለዚህ ይህ ግንዛቤ መወሰድ አለበት፡፡
በሽታው ሁሉንም ሰዉ ያጠቃል፤ በዘር፤ በዕድሜ፤ በጾታ፤ በሀብት፤ ደረጃ ልዩነት የለዉም፡፡ ህጻን፤አዋቂ፤ወጣት፤ በዕድሜ የገፋ፤ ጥቁር፤ ነጭ፤ ሀብታም ደሀ አይለይም፡፡ ልዩነቱ የበለጠ ለሞት የሚጋለጡት በዕድሜ የገፉ በተለይ ከ60 ዓመት በላይ የሆኑ የመሞት ዕድላቸዉ ከፍተኛ ነዉ፤ ሁለተኛዉ ሌላ ተጨማሪ ህመም ካለባቸዉ፤ የልብ ህመም፤ የመተንፈሻ አካል ህመም፤ ደም ግፊት፤ ስኳር፤ በተለያየ ምክንያት በሽታ የመከላከል አቅም የቀነሰ ከሆነ የመሞት ዕድላቸዉ ከፍ ያለ ነዉ፤ ግን በበሽታ የመያዝ ዕድል ሁሉም ሰዉ እኩል ነዉ፡፡

ብዙ መላ ምቶች አሉ፤ አንዳንድ ሰዎች የእግዚአብሔር ቁጣ ነዉ ይላሉ፤ አንዳንዱ በላቦራቶሪ ሆነ ተብሎ የተሰራ ነዉ ይላል::

አመጣጡን በሚመለከት ብዙ መረጃዎች ወደ ሌሊት ወፍ (ወደ አእዋፍ) የሚጠቁሙ አሉ፤ ነገር ግን በደንብ መጠናት አለበት፤ ጥናቱ ገና አላለቀም፡፡ ቻይና ዉሀን ከተማ በሚገኘዉ የተለያዩ የስጋ ምርት በሚሸጡ ሱፐር ማርኬት ዉስጥ እንደተነሳ መረጃዎች ያወሳሉ፡፡ እንደዚህ ዓይነት ቫይረሶች ሲነሱ ሐያላን ሀገራት እርስበርስ ሊወነጃጀሉ ይችላሉ(ቻይና ቫይረሱን የአሜሪካ ወታደሮች አመጡ አሜሪካ ደግሞ የቻይና ቫይረስ ነዉ የመሳሰሉ) ፤ ነገር ግን ይህ በሳይንስ የተረጋገጠ ነገር ያነሳሉ ማለት አይደለም፡፡   

ችግራችን ኮሮና ብቻ አይደለም፡፡ የሁሉም ሰዉ ትኩረት ወደ ኮሮና ብቻ ሲሆን ሌሎች ቀዉሶች፤ የኢኮኖሚ ቀዉሶች እንዲሁም ሌሎች በሽታዎችም አሉ፡፡ ስለዚህ የምንወስናቸዉ ዉሳኔዎች ብዙ ነገሮችን ታሳቢ ያረገና ሚዛናዊ መሆን አለበት፡፡ በረራ በሚመለከት እንደ ጤና ሚኒስተር እኛም ምን መደረግ አለበት የሚለውን ብዙ ሀሳብ አንስተን ስንከራከር ነበር፤ በርግጥ ብዙ ሀገራት ቶሎ በረራ ያቆሙ ነበሩ እነዚህ ሀገራት ደግሞ በኢኮኖሚም የተሻሉና በኢኮኖሚ ቀዉስ ቶሎ የማይጎዱ ናቸዉ፤ ይህ ግን በኛ ሀገር ሁኔታ በጣም ከባድ ነዉ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለምን ከአፍሪካ ጋር የሚያገናኝ ነዉ፤ አቁመን ቢሆን ኖሮ አሁን ከቻይና የምናገኘዉን ድጋፍ ላናገኝ አንችላለን፤ ነገር ግን በረራ ለማቆም ትንሽ ዘገይተናል ብየ አስባለሁ፡፡

የምንወስናቸዉ ዉሳኔዎች ሚዛናዊ መሆን አለበት ግን በረራ ለማቆም ትንሽ ዘገይተናል ብየ አስባለሁ፡፡ ትልቁ ነገር የተደረገዉ ከዉጪ ሲገቡ ሰዎቹን ለመለየት ሞክረናል፤ ከዛ አምልጦ የገባ ሰዉ አልነበረም፤ ሀገር ዉስጥ ከገቡ በኋላ ነዉ ምልክት ማሳየት የጀመሩት፡፡ ለላዉ ቻይናን ለመዝጋት ባሰብንበት ሰዓት ሌላ ሀገርም በሽታዉ ተዳርሰዉ ስለነበር እንድሁም በሌላ መንገድም የመግባት ዕድል ነበር፡፡ አሁንም ያለዉ ጊዜ አልረፈደም ብዙ በረራዎች ተዘግተዋል፤ በተጨማርም የኢኮኖሚና የዲፕሎማሲ ጉዳይም አደጋ ዉስጥ ሳይገባ መወሰን ያለባቸዉ ጉዳዮች አሉ፡፡

ቫይረሱ መጀመሪያ የጀመረባቸዉና የተሰራጨባቸዉ የእስያ ሀገራት እንደ አዉሮፓና አሜሪካ አልተጠቁም፤ የተቀረዉ ዓለም ከቻይና፤ ከሆንግ ኮንግ፤ከደቡብ ኮሪያ፤ከስንጋፖር ከታይዋን መማር ያለባቸዉ ጠንካራ ልምዶች አሉ፤ እነዚህም ለመከላከል የወሰዷቸዉ ጠንካራ እርምጃወች ናቸዉ፡፡ እነዚህ እርምጃዎች ከጅምሩ ጀምሮ ብወሰዱ ጥሩ ነበሩ፤ ዛሬም ግን አልረፈደም፤ ነገር ግን ደሀ ሀገር ከመሆናችን አንጻር የአቅም ዉስንነት አለን፤ ምርመራ መሳሪያዎችን ጨምረዉ ሁሉም ከዉጭ ሀገር ነዉ የሚመጡት፤ ያ ዉስንነት እንዳሌ ሆኖ፤ ወረርሽኝ ለመከላከል የሚያስችል አቅማችን እየተሻሻለ መቷል፤ የምርመራ አቅማችን ብዙ መሻሻል አለበት፤ እንደ ደቡብ ኮሪያ በቀን ፲፣000 ሰዉ ይመረምራሉ፤ እኛ ገና ፲፻ አከባቢ ነዉ፤ የምርመራ አቅማችንን ካሳደግን ብዙ ለማግኘትና የበሽታዉን ምንጭ ለመለየት ይረዳል፡፡ በሽታ ያለበትን ሰዉ አዉቀህ እሱን ገለል ስታረግ ነዉ ሌላዉን እንዳይያዝ ማድረግ የሚትችለዉ፤ ስለዚህ የምርመራ አቀም ማሳደግ የመንግስት ቀዳሚ ትኩረት መሆን አለበት፡፡ እይታችንን በማስፋት የመተንፈሻ አካል በሽታ ምልክት ያላቸዉንና ተጋላጭ ናቸዉ ብለን የምናስባቸዉን አቅማችንን አሳድገን በሙሉ ብንመረምር የተሻለ ነዉ፡፡
ሌላዉ ወሳኝ ነገር ለባለሙያዎች በሽታ ለመከላከል የሚረዱ ቁሳቁሶች፤ ግብዓቶች እንድሁም ዕዉቀት በሚመለከት ዉስንነት አለ፤ ባደጉ ሀገራትም ጭምር በቂ የሆነ በሽታ መከላከያ ቁሳቁሶችን ከባለሙያ አላቀረቡም ተብለዉ ይወቀሳሉ፡፡ ጤና ሚኒስቴር ይህንን ለማሟላት ጥረት እያደረገ ነዉ፤ ይህ ከፍተኛ ጥረትና አቅም የሚጠይቅ ጉዳይ ነዉ፡፡ በኛ ደረጃ በጣም የተሻለ አማራች የሚሆነዉ ብዙ ሰዉ እንዳይታመም ማድረግ ነዉ፤ ይህን ማድረግ ከቻልን የግብአት ፍላጎት ይቀንሳል፡፡
መሪዎችም ጭምር ሁሉም ሰዉ ስራ ስንሰራ ተገብዉን ጥንቃቄ ካላረግን መሪዎችንም ጭምር የማጣት ዕድል ስለሚኖር ጥንቃቄ ያስፈልጋል፡፡

 

በመጀመሪያ ተጨማሪ ለማድረግ ያህል፤ የምርመራ አቅማችንን ለማሳደግ በጤና ሚኒስቴር በኩል ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነዉ፤ ማስክና ሳንታዘር በሀገር ዉስጥ በስፋት እየተመረተ ነዉ፡፡ ለጤና ባለሙያዎቻችን በሽታ ለመከላከል የሚረዱ ቁሳቁሶች አሁን ባለዉ ሁኔታ በቂ አይደለም ግን ለማሟላት ጥረት እየተደረገ ነዉ፤ ቁሳቁሶችን ሁሉም ሀገራት ስለምፈላጉ ለማግኘት የሚወስደዉ ጊዜ ቀላል አለመሆኑ ግንዛቤ መወሰድ አለበት፡፡
ሌላዉ በሀገር ደረጃ የተለያዩ ኮሚቴና ግብረ ሀይል የተቋቋመ ስሆን እስከ ቀበሌ ድረስ መረጃ ለህብረተሰቡ ለመስጠት የምሰራ ግብረ ሀይል አለ፤ ዋናዉ ነገር ይህ በሽታ እንዳይከሰት መስራት አለብን፤ እንደሌሎች ሀገራት በሽህዎች የሚከሰት ከሆነ የማከም አቅም የለንም፡፡ መልእክቶችን ከፕረስ ሰክረተሪያት ጋር በመሆን በጤና ሚኒስቴር አዘጋጅተን ወደ ክልሎች እናወርዳለን፤ ከክልሎች በየሁለት ሳምንት ህብረተሰቡ ጋ ስላለዉ ለዉጥ ስብሰባ አለን፤ ክልሎች ለዞን፤ ዞን ለወረዳ፤ ወረዳ ለቀበሌ ያወርዳል፤ ለላዉ ገጠር በየገበያ ቦታዎች እየዞሩ በሞንታሪቦ ያስተምራሉ፤ ቤት ለቤት ትምህርት እየተሰጠ ነዉ፤በየወረዳዉ ያሉ ሁሉም አመራሮች እየተሳተፉ ነዉ፤ አሁንም ብሆን የገጠር ህብረተሰብ በቂ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ተጨማሪ ስራ ይጠይቃል፡፡

የኤድስ በሽታ አለም ላይ በተከሰተ ጊዜ ገዳይ እንደሆነ መድሐኒት የሌለው እንደሆነ የተዋወቀበት መንገድ ሰዎች ዛሬም ድረስ መገለልን መድሎን ፍርሃትን እንዲያስተናግዱ አድርጓል::  በሽታው ያለባቸው ሰዎች ኣሁንም ድረስ አይናገሩም:: ሰው ሲደነግጥ ወደሚያውቀው ይሄዳል; ሰዎች ኮሮና መድሐኒት የለውም ብዙ ሰዎች እየገደለ ነው ሲባሉ ወደሚያውቁት ይሄዳሉ; ፈዋሽነታቸው ወዳልተረጋገጠ ባህላዊ መድሐኒቶችን: ነጭ ሽንኩርት: ፌጦ ወደመጠቀም; ወደቤተ እምነት ሄዶ መሰብሰብ የመሳሰሉትን ይመርጣሉ::

ከዚህ የምንወጣው ትክክለኛ መረጃ በመስጠት ነው; ችግሩ በዋናነት የመድሐኒት መኖር አለመኖር ሳይሆን ብዙ ሰው በአንድ ጊዜ ቢታመም ማከም አለመቻሉ ነው;ያደጉት ሃገራት የጤና ተቋማት ማከም ያልቻሉትን የኛ ሃገር አቅም በጣም ውስን ነው:: በሽታው የጉንፋን ቤተሰብ ነው; ስለዚህ ማድረግ የምንችለውን በማድረግ እራሳችን በሽታውን ለማስቆም  እንደምንችል ማወቅ::

ሰዎች የተሻለ የንጽህና አጠባበቅ እንዲሁም ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ እንዲኖራቸው እያደረገ ነው:: ብዙ ሰዎች ስራቸውን ከቤታቸው ሆነው ማከናወን እንደሚችሉ ተረድተዋል::  ከዚህ በተጨማሪም ቴክኖሎጂን በመጠቀም ከምንወዳቸው እና ከስራ ባልደረቦቻችን ጋር እንዴት ግንኙነታችንን መቀጠል እንደምንችል ተምረናል

በሽታ የሰው ልጅ አካል በደህና ቀን ከሚያሳየው የተለየ እንዲያሳይ የሚያደርግ ነው::  አንዳንዱ በሽታ ቶሎ ምልክት አይሰጥም: ምልክት ሳይሰጥ ከፍተኛ ደረጃ ሊደርስ ይችላል: ለምሳሌ ካንሰር ደም ግፊት::

ኮቪድ 19 ሁሉም ሰው ላይ አንድ አይነት ህመም የለውም; በሽታው ይይዘናል ግን ህመማችን ይለያያል; ሁሉም ሰው እኩል የመያዝ እድል አለው::  ሰዎች ከሌላ ቦታ ይዘውት ይመጣሉ የህመሙን ምልክት ካሳዩ ይለያሉ: ከነሱ በንክኪ የሚይዘው ሰው ይኖራል:: የቫይረሱ ስርጭት በማህበረሰቡ ውስጥ እየተስፋፋ ከሄደ ማን ከማን እንደያዘው በማይታወቅ ሁኔታ ይስፋፋል; በሽታው በማህበረሰቡ ውስጥ ከተስፋፋ ደግሞ የአንድ ሃገር የጤና ስርዓትን ይሰባብራል:: ጣልያን ከዓለም ሃገራት መካከል በጤና ስርዓቷ 2ኛ ናት (WHO) እንደዚህ ጠንካረ የጤና ስርዓት ያላትን ሃገር በሽታው በዚህ ደረጃ ከፈተን የኛን ሃገር (በዓለም የጤና ስርዓት 189)ምን ሊያደርግ እንደሚችል ማሰብ አይከብድም::

የመከላከያ መንግዶችን ተግብሩ የሚባለው በሽታው በማህብረሰቡ ውስጥ እንዳይስፋፋ ነው; በአንድ ጊዜ ብዙ ሰው እንዳይታመም ነው::

ለምሳሌ የሚከተለውን ስሌት ማየት ይቻላል:

100 ሰው ቢያዝ   80 የሚሆኑት ሃኪም ጋር ሳይሄዱ ይድናሉ

20 የሚሆኑት ሃኪም ዘንድ መሄድ አለባቸው

5/6 የሚሆኑት የጽኑ ህሙማን ክፍል ገበተው ለመተንፈስ የቬንቲሌተር ድጋፍ ይሻሉ; 1 ሰው ይሞታል ከነዚህ መካከል

14/15 ሰው የሚሆኑት ደግሞ የኦክስጂን ድጋፍ ይፈልጋሉ

ይሄ ጠንካራ የጤና ስርዓት ባላቸው ሃገራት ነው; የኛ ሃገር የጤና ስርዓት ጥቂት ግብዓቶች ያለው በመሆኑ ብዙ ሰው ባንድ ጊዜ ቢታመም

ለማስተናገድ አይችልም ብዙ ዋጋ ያስከፍለናል::

በሽታው በመጀመሪያ ሊጎዳ የሚችለው ለበሽታው ተጋላጭ የሚሆኑትን የጤና ባለሙያዎችን ነው:: ብዙ ስልጣኔዎች በወረርሽኝ ነው የፈራረሱት; ስለሆነም እያንዳንዱ ሰው ሃላፊነት አለበት:: እጃችንን የት ጋር እንዳለ መከታተል; የነካነው ነገር ካለ መታጠብ; ፊታችንን አለመንካት: እራሳችን እንዳንታመም ወደምንወዳቸውም እንዳናስተላልፍ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ; አንዳችን ለሌላችን ስለምናስብ መራራቅ በአካል  መጠንቀቅ: ይሄንን የምናደርገው ማህበራዊ  ትስስራችን ነገ እንዲቀጥል ነው:: በሽታው ትልልቅ ሰዎች ላይ ስለሚበረታ በሽታን ይዘን በእምነት ተቋማት ወደሚገኙ አባቶች መሄድ የለብንም ; ይሄንን የምናደርገው ነገ አባቶች ቆይተው እምነታችን እንዲቀጥል ነው ወደ ክፍለሃገር ባለመሄድ የገጠሩ ማህበረሰብ ጋር እንዳናስተላልፍ መጠንቀቅ አለብን::

መተማመን በህዝበና መንግስት መካከል;ህዝብ የሚያምናቸው ተቋማት መኖር;የሚታመኑ የሃይማኖት መሪዎች; የሚታመኑ የጤና ተቋማት;የሚታመን ሚዲያ መኖር ኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል ወሳኝ ነው::

ግልጽነትን በተከተለ ሁኔታ ለህዝቡ ስለበሽታው ያሉ መረጃዎችን ማስተላለፍ: ማህበረሰቡ በዚህ ወቅት የሚሰጠውን መመሪያ በትህትና ቢተገብረው አይጎዳም; ማድረግ የምንችለውን ነገር ማድረግ ትህትና ነው:: እጃችንን መታጠብ እርቀታችንን መጠበቅ በቤት ውስጥ መቀመጥ

የኮሮና በሽታ ሰዎችን በአካል እንዳይቀራረቡ የሚያደርግ ነው፤ በሽታው በዋናነት ያጠቃቸው ሃገራት ማህበረሰባቸው በጣም ተቀራርቦ በህብረት የሚኖርባቸው ናቸው አሜሪካ ስፔን ጣልያን፡፡ በሌላ በኩል ማህበረሰባቸው ተራርቆ ብዙም የጠበቀ ማህበራዊ ህይወት በሌላቸው ሃገራት በሽታው ብዙም አልተሰራጨም ለምሳሌ ስካንዴኔቭያን ሃገራት፡፡ ከዚህ በመነሳት የኛም ሃገር ማህበረሰቡ በጠንካራ ማህበራዊ ህይወት የተሳሰር ስለሆነ ለበሽታው ስርጭት የተመቸ ይሆናል፡፡ ስለሆነም ይህንኑ በመረዳት ከሌሎች ሃገራት በመማር በሽታውን ለመከላከል የሚያስፈልጉ እርምጃዎችን በመውሰድ ወረርሽኙን መከላከል ያስፈልጋል፡፡ ይሄ በሽታ እኛም ሃገር ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል ማሰብ ይገባል፤ የሩቅ አድርጎ ማሰብ አይገባም::

እንደሃገር በየትኛውም መስክ ብቁ ባለሙያዎች የሉንም:: ይሄንን ወረርሽኝ ተከትሎ የጤና ባለሙያዎችን ማዘጋጀት ላይ ስንሆን: ቅጥሮች እየተከናወኑ ነው በፌደራልም በክልልም: በፈቃደኝነት ማገልገል የሚፈልጉ: ጡረታ የወጡና እንዲሁም የስራ ልምምድ ላይ ያሉ ተማሪዎች ተመዝግበዋል:: ከቅጥር በኋላ ስለበሽታው ስልጠና ይሰጣቸዋል: እንዲሁም ሱፐርቪዥን እና ሜንተርሺፕ የሚሰጡ ባለሙያዎች አሉ::

ከተለያየ የህክምና ዘርፍ የተውጣጡ ባለሙያዎች ያሉባቸው 7 ግብረ ሃይሎች ተቋቁመው እየሰሩ ነው:: እንዲሁም ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ ስፔሻሊስት ሃኪሞች በለይቶ ማቆያዎች ድጋፍ በመስጠት ላይ ሲሆኑ፥ኮቪድ – 19ን ለመከላከል እንደሃገር ልንሰራ የሚገባውን የሚያሳይ መመሪያም አዘጋጅተዋል::

ከኢትዮጵያ መድን ኢንሹራንስ የመድን ዋስትና የህይወት ኢንሹራንስ እየተዘጋጀ ነው:: ትራንስፖርትን በተመለከተ ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ራሱን የቻል አገልግሎት ለጤና ባለሙያዎች ተዘጋጅቷል:: ሌሎች ማበረታቻዎችን በተመለከተ ውይይት እየተካሄደ ነው::