ተጨማሪ ኮቪድ - 19
በኮቪድ - 19 ወረርሽኝ ወቅት እንዴት ከቤትዎ በደህና ወጥተው እንደሚገቡ
እንደአጠቃላይ በዚህ የኮቪድ – 19 ወረርሽኝ ወቅት ከቤትዎ እንዳይወጡ ይመከራሉ፡፡
ሆስፒታል ፋርማሲ ወይም ግሮሰሪ ለመሄድ ካልሆነ በስተቀር አብዛኞቹ ከቤት የመውጣት ምክንያቶች አላስፈላጊ ናቸው፡፡
ልብስ ጫማ አሻንጉሊቶች የመሳሰሉትን ለመግዛት ገበያ መውጣት አያስፈልግም፡፡
የሚከተለውን ግሮሰሪ ሆስፒታል ወይም ፋርማሲ ሲወጡ ሊከተሉት የሚገባ መመሪያ ይከታተሉ፡፡
ወደ መደብሮች ገበያ ሆስፒታል እና ፋርማሲ ከመሄድዎ በፊት

1. መውጣት የግድ ያስፈልግሃል?
በተቻለ በቤትዎ እንዲቆዩ ይመከራሉ መውጣት ካለብዎት ግን ወደ መደብሮች ወይም ገበያ የሚያደርጉትን ምልልስ ይገድቡ፡፡
ጥቂት ነገሮች ካስፈለጉ በቤትዎ ባለው ለመቆየት ጥረት ያድርጉና ሲወጡ በአንድ ጊዜ በዛ ያለ ገበያ ያከናውኑ፡፡
ከተቻለ ለሳምንት ወይም ሁለት ሳምንት የሚሆን ምግብ ገዝተው ያስቀምጡ፡፡ ይሄን ለማድረግ ቀድሞ ማቀድን የሚጠይቅ ሲሆን ከቫይረሱ ስጋት አንፃር ይሄን ማድረግ ተመራጭ ነው፡፡ወደሆስፒታል ወይም ክሊኒክ ለቼካፕ የሚያደርጉትን ጉዞም በተመሳሳይ ይገድቡ፡፡ የግድ የሚያስፈልጉ መድሐኒቶችን ለማግኘት በቻ ወደፋርማሲ ወይም ክሊኒክ ይውጡ፡፡
2. መግዛት የሚፈልጓቸውን ነገሮች ዝርዝር ያዘጋጁ
መግዛት የሚፈልጓቸውን ነገሮች ዝርዝር ማዘጋጀት ወደግሮሰሪ ወይም ፋርማሲ የሚያደርጉትን ምልልስ እንዲቀንሱ ከመርዳቱም ባሻገር በሄዱበት ገበያ የሚያሳልፉትን ጊዜ ይቆጥብልዎታል፥ በዚህም በራስዎም ሆነ በሌሎች ሊደርስ የሚችለውን በቫይረሱ የመያዝ ስጋት ያስወግዳሉ፡፡


3. የቤት ለቤት የምግብ ግብዓቶችና ምግብ ግብይት አገልግሎት ይጠቀሙ፡
የሚፈልጉትን ግብዓቶች በቤትዎ እዲመጣልዎ ማድረግ ወደ መደብሮች የሚሄደዉን እና ዕቃ የሚነካካዉን ሰዉ ቁጥር ይቀንሳሉ፤ እንዲሁም አካላዊ ርቀትዎን መጠበቅ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም በቫይረሱ ተይዘዉ ምልክት ከማያሳዩ ሰዎች የኮቪድ-19 ስርጭት እንዲቀንስ ይረዳል፡፡ የምግብ እና የሸቀጣሸቀጥ የቤት ለቤት አገልግሎት የሚሰጡ ተቅዋማት አማራጮችን በመጠቀም የሚፈልጉትን ነገር በማዘዘዝ ቤትዎ ድረስ እንዲመጣልዎ ማድረግ ይችላሉ፡፡ይሁን እንጅ የመድኃኒት የቤትለቤት አገልግሎት እንዲሁም በኢትዮጵያ መደበኛ የሆነ የድልክ ህክምና የሚሰጥ ሆስፒታል የለም፡፡
4. የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ የጥንቃቄ እርምጃዎችን ተግባራዊ ያደረገ ሆስፒታል ፣ ፋርማሲ ወይም የሸቀጣሸቀጥ መደብር ይምረጡ
ለምሳሌ ፣ በመግቢያ በር ላይ እንደ ሳሙና እና ውሃ የመሳሰሉት የእጅ መታጠቢያ ቁሳቁሶችን ወይንም የአልኮል መጠኑ ከ60% በላይ የሆኑ የእጅ ማጽጃ ሳኒታይዘር አቅርቦ ለደምበኛ አገልግሎት የሚሰጥ ሆስፒታል ፣ ፋርማሲ ወይም የሸቀጣሸቀጥ መደብር በመፈለግ ይጠቀሙ፡፡ በአሁኑ ጊዜ አብዛኛዉ እንደ ምግብ ቤቶች ፣ ባንኮች ፣ የገቢያ አዳራሾች እና የሸቀጣሸቀጥ ሱቆች ያሉ የንግድ ተቅዋማት በመግቢያ በራቸዉ ላይ የእጅ መታጠቢያ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡.


5. ወደ መደብሮች ፣ ፋርማሲዎች እና ሆስፒታሎች ለመሄድ ሲያስቡ ሰዉ በብዛት በማይኖርበት ጊዜ ለመሄድ ይሞክሩ
አብዛኛውን ጊዜ ጠዋት ጠዋት መደብሮች ፣ ፋርማሲዎች እና ሆስፒታሎች ከሞላ ጎደል ባዶ የመሆን ባሃሪ አላቸዉ፡፡ በምትገዣዡበት ጊዤ የተለያዩ ሱቆችን/መደብሮችን ከማሰስ የሚያስፈልገውትንና የሚችሉትን ያህል እቃ ከአንድ ሱቅ/መደብር መግዛት ይመከራል፡፡ ዓመት በዓላ በሚኖርበት ጊዤ ዓመት በዓሉ ከመድረሱ ከበቂ ቀናት በፊት የሚያስፈልገውትን አስፔዛ በመገዛዛት የባዕል ዋዜማ የገበያ ግርግርን ያምልጡ።
6. ወደነዚ ቦታዎች ለብቻዎት ይሂዱ
በተቻለ መጠን አንድ ወይም የተወሰነ ሰው ብቻ ወደ ገበያ መሄድ ይኖርበታል። ይህ በቤተሰብዎ ውስጥ ለኮቪድ-19 ተጋላጭ ሊሆኑ የሚችሉትን የሰዉ መጠን ከመቀነስም በተጨማሪ በገበያ ማዕከል ያለዉን የሰዉ ጫና በመቀነስ ማሕበራዊ ርቀትን ጠብቆ ለመገበያይት አስተዋዖ ያደርጋል። ህዓናትንና ለኮቪድ-19 ተጋላጭ የሆኑትን ሰዎች ከቤት ይተዉ። በተመሳሳይም ወደ ፋርማሲዎች እና ሆስፒታሎች የተወሰነ አስፈላጊ ሰው ብቻ እንዲሄድ ያድርጉ።


7. ለብቻዎ ይጓዙ
ከተቻለ ሆስፒታል ፣ ፋርማሲ ወይም የሸቀጣሸቀጥ መደብር በሚመላለሱበት ጊዜ የራስዎን መኪና ይጠቀሙ፡፡ የግል መኪና ከሌልዎት በእግሮ መሄድን እንደአማራጭ ይጠቀሙ፡፡ ይሄም ጥሩ አማራጭ ሆኖ ካልታዮት ማሕበራዊ ርቀትን በመጠበቅ የህዝብ ማመላለሻን ሰዉ በብዣት በማይኖርበት ጊዜ ይጠቀሙ፡፡
8. የበሽታዉ ምልክቶች ከታዩ ከቤት እንዳይወጡ
ትኩሳት ፣ ሳል ወይም የትንፋሽ እጥረት ካጋጠሙ ወይም ለቫይረሱ የተጋለጡ እንደሆኑ ከተሰማዎት ቤት መቆየት እና በቤት ውስጥ ማህበራዊ ርቀትን በመጠበቅ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ወደ ገበያ ማዕከል ወይም ወደ ፋርማሲ መሄድ ካስፈለግዎ ጓደኛዎን ፣ የቅርብ ቤተሰብዎን ፣ ወይም ሌላ ሰው የሚያስፈልገዎትን ገዝቶዎሎት ከቤቶ በር እንዲያስቀምጥሎት ያድርጉ ፡፡
ወደ ሆስፒታል መሄድ የሚያስፈልግዎ ከሆነ በማንኛዉም ጊዜ የፊት ማስክ ማድረግ ፣ በሚያስነጥሱበት ወይም በሚያስሉበት ጊዜ አፍና አፍንጫዎትን በክንድ መሸፈን፣ ፊትዎን አለመንካት፣ እና እጅን መታጠብ በጭራሽ አይዘናጉ፡፡

ሆስፒታል፣ፋርማሲ ወይም ሱቅ ሲገቡ

1. እጆችዎን ደጋግመው ያፅዱ
ወደ ሆስፒታል ሱቅ ወይም ፋርማሲ ከመግባትዎ በፊት የእጅ ማፅጃን ይጠቀሙ፣ከወጡ በኋላ እንደገና ይጠቀሙት። በሱቁ ውስጥ እያሉ በተቻለ መጠን ጥቂት ነገሮችን ለመንካት ይሞክሩ
(የግል ንብረቶችን ጨምሮ)። ስልክዎን ወይም ሌሎች የግል ንብረቶችን ከነኩ ከሱቁ ፣ ፋርማሲው ወይም ሆስፒታሉ ሲወጡ በአግባቡ ያፅዱዋቸው።
2. አፍንጫዎን እና አፍዎን በጭምብል ይሸፍኑ
በሕዝብ ቦታዎች ውስጥ ማንኛውም የጨርቅ ጭንብል እንዲለብስ ይመከራል። ጭምብል ከሌለዎት አፍንጫዎን እና አፍዎን በሌላ ጨርቅ (እንደሻርፕ) ይሸፍኑ፡፡ ጭምብሉ በትክክል መደረጉን ያረጋግጡ። ትክክለኛ የጭንብል አለባበስ እና አወላለቅ መረጃ እዚህ ይገኛል።የፊት ጭንብል መጠቀም የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ ያስችላል። ማህበራዊ ርቀት ቢጠብቁም እንኳ የፊት ጭንብል ጥቅም ላይ መዋል አለበት።


3. ማህበራዊ ርቀት ይጠብቁ
የ 2 ሜትር ርቀት በማንኛውም የህዝብ ቦታ መጠበቅ አለበት፡፡ ምንም እንኳን ብዙ ሰዎች ባሉባቸው ገበያዎች ውስጥ ይህ አስቸጋሪ ቢሆንም ፣ ርቀትዎን ለመጠበቅ ይሞክሩ፡፡የሆስፒታል ማቆያ ክፍል ወንበሮች ብዙውን ጊዜ የ2 ሜትር ርቀት የማይጠብቁ ስለሆኑ ጥግ ላይ መቆም ወይም ከቤት ውጭ መጠበቅ ሊኖርብዎ ይችላል፡፡
4. ወረፋ እየጠበቁ እያለ አንድ ሰው በጣም ቅርብ ከሆነ ወደ ኋላ እንዲመለስለ መጠየቅ አይፍሩ
በአብዛኛዎቹ መደብሮች እና ፋርማሲዎች ሰዎች ወረፋ እየያዙ እያለ የት መቆም እንዳለባቸው የሚያሳዩ ምልክቶች አሉ፡፡ ሆኖም በመደብሮች ፣ በፋርማሲዎች ወይም በሆስፒታሎች ውስጥ ሰዎች 2 ሜትሩን ላይጠብቁ ይችላሉ። ይህ ከሆነ ይሉኝታ ይዞቱ ፀጥ አይበሉ። ራስዎን ብቻ ሳይሆን ሌሎችን እየጠበቁ ነው፡፡


5. የወለሎችን ንፅህና ይጠብቁ
አዲስ አበባ ውስጥ አብዛኛዎቹ መደብሮች፣ሆስፒታሎች እና ፋርማሲዎች የንጽህና መጠበቂያዎችን አያቀርቡም። ስለዚህ የራስዎን የጽዳት መሳሪያ ለመውሰድ ይሞክሩ፡፡ በሆስፒታል ፣ በፋርማሲ እና በመደብሮች ውስጥ የበር መያዣዎችን ፣ጋሪዎችን እና ስኪሪቢቶችን ለማፅዳት ይጠቀሙበት፡፡ ከተቻለ የራስዎን ስኪሪቢቶ ይውሰዱ ፡፡
6. ሁሉም ወለሎች በሰው እንደተነካኩ ይገምት
ምንም እንኳን አንዳንድ ገጽታዎች ከሌሎቹ የበለጠ የተበከሉ ቢሆኑም ሁሉም ገጽታዎች በበሽተኛ ሰው እንደተነካኩ አድርገው ያስቡ፡፡ ይህ የታሸጉምግቦች ፣ መድኃኒቶች ፣ መቀመጫዎች ወዘተ ያካትታል፡፡ስለዚህ በሱቆች ፣ በፋርማሲዎች እና በሆስፒታሎች ውስጥ ይህንን ያስታውሱ፡፡


6. ለመግዛት ያቀዱትን ብቻ ይንኩ
ኮሮናቫይረስ የሚተላለፍበት አንዱ መንገድ የተበከሉ ነገሮችን በመንካት እና ከዚያ ዓይኖችዎን ፣ አፍንጫዎን እና አፍዎን በመንካት ነው ፡፡ስለሆነም ካልተገደዱ በቀር አንዳች ነገር አይንኩ። ይህ ማለት ለመገምገም ፍራፍሬዎችን እናአትክልቶችን አይንኩ፡፡ በመደብሮች እና በፋርማሲዎች ውስጥ የማይገዙዋቸው ንነገሮች አይንኩ፡፡
7. ጓንት ማድረግ አያስፈልግም
ወደ ውጭ በሚወጡበት ጊዜ ጓንት ማድረግ አስፈላጊ አይደለም ምክንያቱም ያደረጉት ጓንት ልክ እጆቻችን በቫይረሱ ሊበከሉ በሚችሉበት መንገድ ሊበከሉ ስለሚችሉ ነው፡፡ በተጨማሪም ጓንቶችን ማጠባችን እጆቻችንን ከምንታጠበው ያነስ ነው የሚሆነው::
ከዚህ ይልቅ ወደግሮሰሪ ሆስፒታል ወይም ፋርማሲ ከመግባትዎ በፊትና ሲወጡ እጆቻችን በውሃና ሳሙና መታጠብ ወይም ንፅህና መጠበቂያ አልኮል መጠቀም ይመረጣል፡፡ ይህም ሆኖ ጓንት መጠቀም ከፈለጉ ተጠቅመን የምንጥላቸውን አይነትና ወዲያውኑ ማስወገድ ያስፈልጋል፡፡


8. ፊትዎን አይንኩ
የኮሮና ቫይረስ ከአንድ ሰው ወደሌላው ከመተላለፉ በተጨማሪ የተበከሉ ወለሎችን ወይም ቁሶችን በእጆቻችን ነክተን ፊታችንን አፋችንን ወይም አፍንጫችንን መንካት በቫይረሱ እንድንያዝ ያደርገናል፡፡ ስለዚህ አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ምንም ነገር በእጆቻችን ከመንካት መቆጠብ አለብን፡፡
9. በሚያስሉበትና በሚያስነጥሱበት ጊዜ አፍና አፍንጫዎን ይሸፍኑ
በሚያስሉበት ወይም በሚያስነጥሱበት ጊዜ በክንድዎ ይሸፍኑ፥ እንዲሁም ውጪ በሚሆኑበት ጊዜ ጭንብል ሶፍት ወይም መሸፈኛ ስካርፍ ይጠቀሙ፡፡

ቤትዎ ሲመለሱ

1. እጆችዎን ይታጠቡ
የምግብና መድሐኒት ማሸጊያዎችን ከነኩ በሗላ እንዲሁም እቤትዎ እንደደረሱ እጆችዎን መታጠብ ወይም በሳኒታይዘር ማጽዳት እንዳይረሱ፡፡
የበለጠ ጥንቃቄ ለማድረግ ፊትዎን በመታጠብ ቫይረሱ ከፊትዎ ላይ ወደ አፍ አፍንጫ እና አይን እንዳይገባ ያድርጉ፡፡
2. ከውጭ ይዘዋቸው የመጡት ሸቀጦች ወይም መድሐኒቶች ምን ያህል አደጋ ሊያስከትሉ ይችላሉ?
ከቤት በሚወጡበት ጊዜ ትልቁ አደጋ ቫይረሱ ካለበት ሰው ጋር ሊኖር የሚችል ንክኪ ነው፡፡ ነገር ግን ከገበያ ወይም ከፋርማሲ ይዘውት የመጡት እቃ በቫይረሱ ተበክሎ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት ካለዎት የሚከተሉትን እርምጃዎች ይውሰዱ:-
- እቤት እንደደረሱ የምግብ እና መድሀኒት ማሸጊያዎች ከምንም ነገር ጋር ከመነካካታቸው በፊት መጥረግ/ማጽዳት
እንዲሁም እነዚህን ሸቀጦች ያስቀመጡበትን ቦታ በሳኒታይዘር ማጽዳት፡፡ - የገዙትን ሸቀጥ ወደንጹህ መያዣ ካዘዋወሩ በሗላ የሚወገዱ ማሸጊያዎችን መጣል፡፡ ዘምቢል ወይም የጨርቅ ቀረጢቶችን ከተጠቀሙ ሙሉ ለሙሉ በሳኒታይዘር ያጽዱ፡፡
በተጨማሪም የጨርቅ ቀረጢቶችን በልብስ ማጠቢያ ማሽን በውሃና ሳሙና ማጠብ ይችላሉ፡፡ - አንዳንድ ሰዎች የገዛነውን ሸቀጥ ከቤት ውጪ ለ 72 ሰዓታት ብንተወው ቫይረሱን ጉዳት የማያደርስ ያደርገዋል ብለው ይጠቁማሉ፡፡
ሆኖም እንደወተት መድሀኒት ያሉ የሚበላሹ ነገሮችን በሚመከረው የቅዝቃዜ ቦታ ማስቀመጥዎን እንዳይረሱ፡፡ - የገዙዋቸውን እቃዎች ትክክለኛ ቦታቸው ካኖሩ በሗላ እጅዎትን ይታጠቡ፡፡


3. ውሃ የማያሳልፉ ነገሮችን ማጠብ
ፍራፍሬዎችንና አትክልቶችን እስከ 20 ሰከንድ በማጠብ ከቆሻሻና ከፀረ ተባይ መድሀኒቶች ማስለቀቅ በምግብ ከሚመጡ ጀርሞች ይከላከልልናል፡፡ ታዲያ በውሃና ሳሙና ከተጠቀሙ በመጨረሻ በንጹህ ውሃ በደንብ ማጽዳትዎን እንዳይረሱ፡፡
እንዲሁም ውሃ የማያሳልፉ የምግብ የመድሃኒት የመሳሰሉት ማሸጊያዎችንም ማጠብ ይቻላል፡፡
4. ለብሰናቸው ወደውጪ የወጣነው ልብሶች የተለየ ጥንቃቄ ይፈልጋሉ?
ወደ ሆስፒታል ፋርማሲ ወይም መደብሮች የምናደርገው ጉዞ የተገደበ ከሆነ ለልብሳችን የምናደርገው የተለየ ጥንቃቄ ላይኖር ይችላል፡፡
ነገር ግን ከቤት ውጪ በነበርዎት ቆይታ ማህበራዊ እርቀትዎን ካልጠበቁ እንዲሁም ሰዎች በእርስዎ አቅጣጫ ካሳሉ ወይም ካስነጠሱ ወደቤት እንደተመለሱ ልብስዎትን እንዲያጥቡ ይመከራሉ፡፡
እንደአጠቃላይ ግን ቅድሚያ የሚሰጠው ነገር እጆችዎን በተደጋጋሚ መታጠብ ፣ አይናችንን አፍንጫችንን እና አፋችንን አለመንካት፣ ጭንብል ማድረግ ነው፡፡
በኮቪድ- 19 የተያዘን ሰው በቅርብ ሆነው እየተንከባከቡ ከሆነ ግን ልብስዎትን ቶሎ ቶሎ በሳሙናና ውሃ ማጠብ ያስፈልጋል፡፡


5. ጫማዎች በበሽታው ሊበክሉን ይችላሉ?
ጫማዎቻችንን እቤት እንደደረስን በማጽዳት ወይም ከቤት ውጪ በመተው ተጨማሪ የጥንቃቄ እርምጃዎችን መውሰድ ተገቢ ነዉ፡፡
6. ወደባንኮች በአካል ከመሄድ ይልቅ ኤቲኤም ወይም ሞባይል ባንኪንግ መጠቀም
ኮቪድ -19 ቀጥታ በቆዳችን በኩል ገብቶ አይዘንም ይልቁንም እጆቻችንን ከኣይናችን ከአፍንጫችን እና አይኖቻችን ጋር በሚኖራቸው ንክኪ ቫይረሱ ሊይዘን ይችላል፡፡ ቫይረሱ ከብር ወይም ሳንቲም በሚኖረን ንክኪ ለመተላለፉ የተረጋገጠ ነገር ባይኖርም ከማንኛውም ቁስ ጋር ንክኪ ካደረግን በሗላ እጆቻችን ማጽዳት መርሳት የለብንም፡፡ የገንዘብ ንክኪንም ለመቀነስ ኦንላይን የገንዘብ ማስተላለፊያ መንገዶችን መጠቀም ይመከራል፡፡


7) ኮሮና ቫይረስ በብር ወይም በሳንቲም ሊተላለፍብን ይችላል?
ኮቪድ – 19 ከሰው ወደሰው ከመተላለፉ በተጨማሪ የተበከሉ ወለሎችን ወይም ቁሶችን በእጆቻችን ነክተን አፋችንን አይናችንን ወይም አፍንጫችንን ስንነካ ቫይረሱ ሊይዘን ይችላል፡፡ ስለሆነም ምንም ነገር ግድ ካልሆነ በስተቀር መንካት የለብንም፡፡ በገበያም ልንገዛ ያላሰብነውን ነገር መነካካት የለብንም
በኮንዶሚኒየም እና አፓርትመንቶች የሚኖሩ ሊያደርጉት የሚገባ:-
- በተደጋጋሚ የውሃ መቋረጥ ስለሚከሰት በተለይ ከፍ ያለ ወለል ላይ ያሉ ነዋሪዎች ተጨማሪ ውሃ የእጅ ማጽጃ ሳኒታይዘር አልኮል እና ሌሎችንም የንጽህና መጠበቂያዎች አጠራቅመው እንዲይዙ ይመከራል፡፡
- በኮንዶሚኒየሞችና አንዳንድ አፓርትመንቶች የጋራ የሆኑ በእጅ ልብስ ማጠቢያ ቦታዎች አሉ፡፡ እነዚህን ቦታዎች በምትጠቀሙበት ጊዜ አካላዊ እርቀታችሁን ጠብቃችሁ መሆን አለበት፡፡
- ከቤተሰቡ ጋር የማይኖሩ የቤት ውስጥ ሰራተኞችን የሚጠቀሙ ነዋሪዎች ሰራተኞቻቸው አካላዊ እርቀታቸውን እንዲጠብቁ ጭንብል እንዲያደርጉ እንዲሁም ሲገቡና ሲወጡ እጃቸውን እንዲታጠቡ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
- መኪና ያላቸው ነዋሪዎች በዚህ ጊዜ መኪኖቻቸውን በመንገድ ላይ ከማሳጠብ ይልቅ እራሳቸው እንዲያጥቡ ይመከራል፡፡