ስለ ኮቪድ-19 ነገሮች

ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ - 19) ምንድነው?

የበሽታው ስያሜ COronaVIrus Disease 2019 ወይንም ኮቪድ-19 ሲሆን, የበሽታው አምጪ ቫይረስ Severe Acute Respiratory Syndrome Coronavirus 2 (SARS – CoV2) ተብሎ ይታወቃል::

‘ኮሮና’ የላቲን ቃል ሲሆን ዘውድ ማለት ነው:: ኮሮና ቫይረስ በሽታው የሚገኝበትን የቫይረስ ቤተሰብ የሚያመለክት ሲሆን ዘውድ መሰል ቅርጽ ስላለው የተሰጠ ስያሜ ነው::

የተለያዩ የኮሮና ቫይረስ አይነቶች ሲኖሩ እነዚህም ጉንፋን MERS (Middle East Respiratory Syndrome) እና SARS (Severe Acute Respiratory Syndrome) የመሳሰሉት ናቸዉ ::

ኮቪድ-19 በቅርቡ የተከሰተ ሲሆን የሰው ልጆች የመተንፈሻ አካል የሚያጠቃ በሽታ ነው::

ቫይረሱ በሰውነታችን ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራል?

1

ቫይረሱ ወደሰውነታችን በአፋችን፥ በአይናችን ወይም በአፍንጫችን ይገባል

2

ቫይረሱ ወደ ሰዉነታችን ከገባ በኃላ፤ ወደ ኋለኛዉ አፍንጫችን ክፍልና ወደ ጎሮሮ ስስ ሽፋንጋ /mucous membranes/ይሰራጫል፡፡ይዛመታል፡፡

3

ዘውድ በሚመስሉ ነጠብጣቦች አማካኝነት የሰውነታችን ሴሎች ውስጥ ይገባል:: በዚህም የሰውነታችንን በሽታ የመዋጋት አቅም በመጉዳት ራሱን እያባዛ ሰውነታችንን መቆጣጠሩን ይቀጥላል::

4

4

ከዚያም ቫይረሱ ከጉሮሮ ጀርባ ወደታች ወደ ብሮንኪያል ቲዩብስና/bronchial tubes/ ወደ ሳንባ ይወርዳል፡፡  የመተንፈሻ ሽፈንንም ይጎዳል፤ እብጠትም ያስከትላል፡፡

ኢንፌክሽኑ በጣም የከፋ ከሆነ የአየር መተላለፊያ ሽፋን አልፎ ወደአየር መተላለፊያው መጨረሻ ወደሆነው የጋዝ ልውውጥ ክፍሎች ይሄዳል፡፡

5

ሳንባችን ኢንፍላሜሽን የሚፈጥሩ ነገሮችን ወደታችኛው ክፍል ወደሚገኙት የአየር ከረጢቶች በማፍሰስ የሳንባ ምች በመፍጠር ለዚህ ወረራ ምላሽ ይሰጣሉ ፡፡

6

በኢንፍላሜንሽን የተሞላው ሳንባ በደም ፍሰት ውስጥ በቂ ኦክስጅንን ማግኘት አይችልም፡፡ ይህም ኦክስጅንን የመውሰድ አና ካርቦን ዳይኦክሳይድን የማስወገድ ችሎታን ይቀንሳል፡፡ ብዙ የአካል ክፍሎችም በኦክስጂን እጥረት፣ በኢንፍላሜሽን እና septic shock ምክንያት መሥራት ያቆማሉ፡፡

ከቀላል እስከ መካከለኛ ህመም ምልክቶች

ምልክቶቹ ብዙውን ጊዜ የሚጀምሩት በጉሮሮ ፣ ጀርባ ላይ በቆሰለ ጉሮሮ እና በደረቅ ሳል ነው፡፡ የሰውነታችን የመከላከያ ሂደት/immune system/የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚያደርገው ጥረት ትኩሳትን ያስከትላል፡፡

ከፍተኛ ደረጃ ህመም ምልክቶች

የማያቋርጥ ሳል

ይህም ማለት ከአንድ ሰዓት ለሚበልጥ ጊዜ ማሳል፣ ወይም በ24 ሰዓታት ውስጥ 3 ወይም ከዚያ በላይ ጊዜያት ማሳል ነው፡፡ አንድ ግለሰብ አብዛኛውን ጊዜ ሳል ካለው ከወትሮው የከፋ ሊሆን ይችላል፡፡

ከፍተኛ የሆነ ሙቀት

ሰውነታችን ቫየረሱን ለመዋጋት በሚያደርገው ጥረት የሰውነታችን ሙቀት በዛው ልክ ይጨምራል፡፡

የትንፋሽ እጥረት

በሳንባ ውስጥ ያለው ንፍጥ መሰል ሽፋን በአየር መተላለፊያዎች በኩል አየር እንዳይንቀሳቀስ ያደርጋል፤ ይህም መተንፈስን ከባድ ያደርገዋል፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ የትንፋሽ እጥረት፣ የመተንፈስ ችግርና የድካም ስሜት ያስከትላል፡፡

ኮቪድ-19 ምን ያክል ገዳይ ነው?

የተለያዩ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ከሆነ በኮቪድ-19 ከተጠቁት ሰዎች ዉስጥ የህመም ምልክቱ 80 በመቶ ላይ ቀላል በ13 በመቶ ከባድ እና በ6 በመቶ አስከፊ መሆኑን ያሳያል፡፡
ኮቪድ-19 በጣም አስከፊ ካልሆነና ጥቂት የህብረተሰቡን ክፍል ብቻ የሚገድል ከሆነ ታድያ ለምንድዉ በጣም አደገኛ የሚሆነው?
ኮቪድ-19 ከዚህ በፊት ከሚታወቁት እንደ ሳርስ-ኮ፟ቭ እና ሜርስ-ኮ፟ቭ ወረርሽኞች በይበልጥ ፍጥነት እና በቀላሉ የሚዛመት መሆኑ ነው፡፡

እራስዎን ከበሽታው ለመጠበቅ ማድረግ ያለብዎት
ሌሎችን ከበሽታው ለመጠበቅ ማድረግ ያለብዎት

በቤትዎ ይቆዩ

እራስዎትን እና ሌሎችን ከበሽታው ለመጠበቅ ውጤታማው መንገድ በቤት ውስጥ በመቆየትና ከሌሎች ጋር ግንኙነት መቀነስ ነው፡፡

አካላዊ ርቀትን ይለማመዱ

የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከላት በበሽታዉ የመያዝ  አጋጣሚን ለመቀነስ ከሌሎች ሰዎች ቢያንስ የ2 ሜትር ርቀትን እንድንጠብቅ ይመክራል፡፡

ይህ አጭር ቪዲዮ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ምን ያህል የቫይረሱን ስርጭት ዝግተኛ እንደሚያደርገው ያሳያል. 

ከእጅ ንክኪና መጨባበጥ ይቆጠቡ

አንድ ሰው አካላዊ ርቀትን የመጠበቅ ምግባራዊ ሃላፊነቱን ዘንግቶ በበሽታው ከተጠቃ ሰው ጋር ቢቀራረብ ሊያደርግ የሚችለው በጣም መጥፎ ነገር በእጅ ንክኪ ቫይረሱ እንዲሰራጭ ማድረግ ነው፡፡

ሰዎች ሰላም ለመባባል ከንክኪ ውጪ ብዙ ሌሎች አማራጮችን መጠቀም አለባቸው፡፡

በተደጋጋሚ እና በትክክል እጅዎን ይታጠቡ

በተደጋጋሚ እጅን በሳሙና እና በውሀ ለ20 ሰከንድ ያክል መታጠብ እጃችን ላይ ሊኖሩ የሚችሉ የማይታዩ በሽታ አምጪ ተህዋስያንን  ለመግደል ቁልፍ የሆነ የህዝብ ጤና የሚጠብቅ ተግባር ነዉ፡፡

የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ትክክለኛ የእጅ አስተጣጠብን ይከታተሉ: https://www.facebook.com/EthiopiaFMoH/videos/220324276076606/ 

ፊት የመንካት ልምዶትን ያስወግዱ

ቫይረሱ ካለባቸው ሰወች ወይም እቃወች ወደሌለባቸው በእጅ ንክኪ ስለሚተላለፍ እጃችንን ሳንታጠብ አይናችንን አፍንጫችንን አና አፋችንን መንካት የለብንም ፡ ይህ ቫይረሱ ወደ ሰውነታችን እንዲገባ ተጋላጭ ስለሚያደርገን ማስወገድ አለብን፡፡

በሚከተለው የ BBC  ቪዲዮ (https://www.youtube.com/watch?v=2sxI7s8p99o)  ሳይኮሎጂስት Natasha Tiwari እንዴት ፊታችንን በእጃችን የመንካት ልምዳችንን ማስወገድ እንደምንችል ትመክረናለች::

የኮቪድ-19 ምልክቶችን ነቅተው ይከታተሉ

በተለያዩ የመተንፈሻ አካል በሽታዎች መካከል ያለው የበሽታዎች ምልክት መመሳሰል ብዙዎችን በኮሮና በሽታ መያዝ አለመያዛቸውን ለማወቅ አስቸጋሪ አድርጎባቸዋል። የኮቪድ- 19 በሽታ ምልክቶች ከታየብዎት ሌሎች ሰዎችን እንዳይበክሉ የሚከተሉትን ያድርጉ

በቤትዎ ይቆዩ

እራስዎትን እና ሌሎችን ከበሽታው ለመጠበቅ በጣም ውጤታማው መንገድ በቤት ውስጥ በመቆየትና ከሌሎች ጋር ግንኙነት መቀነስ ነው፡፡

 

አካላዊ ርቀትን ይለማመዱ

የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከላት በበሽታዉ የመያዝ  አጋጣሚን ለመቀነስ ከሌሎች ሰዎች ቢያንስ የ2 ሜትር ርቀትን እንድንጠብቅ ይመክራል፡፡

ይህ አጭር ቪዲዮ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ምን ያህል የቫይረሱን ስርጭት ዝግተኛ እንደሚያደርገው ያሳያል. 

የመተንፈሻ አካላት ንጸህናን ይጠብቁ

የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የጉንፋን ነክ በሽታወች ምልክት ያለባቸው ሰዎች ክንዳቸውን ተደግፈዉ እንዲያስሉ ወይም እንዲያስነጥሱ ይመከራል፡፡ የአለም ጤና ድርጅትም ሰዎች ሶፍት በመጠቀም እንዲያስሉ ወይም እንዲያስነጥሱ የተጠቀሙበትንም ሶፍት በስነስርኣት ካስወገዱ በሃላ እጅን በደንብ በሳሙናናበ ዉሃ ለ 20 ሰከንድእንዲታጠቡ ይመክራል፡፡ ይሄ ተግባር ቫይረሱ የሚገኝባቸዉ የሰዉነት ፈሳሽ በራሱ ልብሶች ወይም ሶፍት ላይ እንጂ በሌሎች ቁሳቁስ እና አከባቢው ላይ እንዳይቀመጥ ያስችለዋል ፡፡

 

ጭምብል (face mask) ይልበሱ

በበሽታው ያልተጠቃ ከተጠቃ  ሰው ጋር በቅርበት ከተገናኘ ጭምብል መልበስ በበሽታው የመያዝ እድልን ይቀንሳል፡፡ ከኮቪድ-19 ጋር ሊያያዝ ወይም ላይያያዝ የሚችል የጉንፋን ምልክቶች ያሉበት ሰው ሌሎችን ከበሽታው ለመጠበቅ ጭምብል መልበስ አለበት፡፡

የሚከተለውን ሊንክ በመጫን የፊት ማስክ አጠቃቀምን ይከታተሉ: https://www.facebook.com/EthiopiaFMoH/videos/903512013409901/

 

ከእጅ ንክኪና መጨባበጥ ይቆጠቡ

አንድ ሰው አካላዊ ርቀትን የመጠበቅ ምግባራዊ ሃላፊነቱን ዘንግቶ በበሽታው ከተጠቃ ሰው ጋር ቢቀራረብ ሊያደርግ የሚችለው በጣም መጥፎ ነገር በእጅ ንክኪ ቫይረሱ እንዲሰራጭ ማድረግ ነው፡፡

ሰዎች ሰላም ለመባባል ከንክኪ ውጪ ብዙ ሌሎች አማራጮችን መጠቀም አለባቸው፡፡

በተደጋጋሚ እና በትክክል እጅዎን ይታጠቡ

በተደጋጋሚ እጅን በሳሙና እና በውሀ ለ20 ሰከንድ ያክል መታጠብ እጃችን ላይ ሊኖሩ የሚችሉ ቫይረሶችን ለመግደል ቁልፍ የሆነ የህዝብ ጤና የሚጠብቅ እና የማይታዩ በሽታ አምጪ ተህዋስያንን እንደሚገድል ይታመናል፡፡

የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ትክክለኛ የእጅ አስተጣጠብን ይከታተሉ: https://www.facebook.com/EthiopiaFMoH/videos/220324276076606/ 

ከታመሙ ሊወስዷቸው የሚገቡ እርምጃዎች

እነዚህ ተራ ቁጥር ከ1-5 የተመለከቱት በኢትዮጵያ በሽታዉን ለመከላከል የሚተገበሩ ናቸው፡፡ ከዚህ የተለየ ሁኔታ ሲያጋጥም በአቅራብያችሁ ወዳለው የጤና ባለስልጣን  በመሄድ የበሽታውን ምልክቶች ምርመራ እና መረጃ ማሳወቂያ መመሪያወችን ይጠይቁ፡፡

1. እራስዎትን ለዋና ዋና የኮቪድ-19 ምልክቶች ማለትም ትኩሳት ደረቅ ሳል እና የትንፋሽ ማጠር ካለብዎ ይመርምሩ፡፡

2.ከላይ ከተጠቀሱት ምልክቶች አንዱ ወይም ሁሉም ከተሰማዎት 8335 ደውለው ምልክቶቹን ያሳውቁ፡፡

3.የ8335 ጥሪ ረጅም መጠበቂያ ጊዜ ሊኖረው ሰለሚችል በትዕግስት መስመር ላይ ይጠብቁ፡፡

4.የጥሪ ተቀባዩ ተጨማሪ መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች ካሉ ይወስናል፡፡

5.የጥሪ ተቀባዩ በሽታው አለብዎት ብሎ ካመነ የህመምዎን ሁኔታ ሊያረጋግጥ የሚችል የምርመራ እና ክትትል ቡድን ወደ አከባቢዎ የሚልክ ይሆናል፡፡